Selam here is my Q Result metolgn arif gibi deresegn ena ene be bahire zimtgna ena yilugnta yemiyatkagn sew negn ena gibi sihed endet mashashal albgn or kostara mehon efelgalew? Bizu gize ke ebet timhrt bet Nw wuloye ye bet lij negn ena gibi sihed endet adrge lekuqam mann Nw mamen yalbgn guadgna endet nw memrtew? The last konjo yembal lij negn ena endet ke albale sewoche erasen metbk albgn? Batkalay min timkirugnalachu?
Feb 13, 2023ከአንድ አመት በኋላ ይህን ጥያቄሽን መጥተሽ አንብቢው እሺ። :) በዚሁ እንድትቀጥዪ ምኞቴ ነው። ከክፉ ሰዎችና ተንኮላቸው ሁሉ ጠብቆሽ አላማሽን አሳክተሽ የምትወጪ ያድርግሽ አቦ! ምክር ቁጥር አንድ: በሀይማኖትሽ ጠንከር በይ። ዩኒቨርሲቲ ከገባሽ ወዲህ ብዙ የሚገጥሙሽ ፈተናዎች ይመጣሉ። እነዚህን ፈተናዎች በጽናት ለማለፍ ከፈጣሪሽ ጋር ያለሽ ቅርበት ይወስነዋል። ወደ ፈጣሪሽ እጅሽን በማንሳት ቅረቢው። ምክር ቁጥር ሁለት: ዩኒቨርሲቲ ማለት እውቀት መቅሰሚያ ቦታ እንጂ ከቤተሰብ ተደብቆ እንደፈለጉ የሚሆኑበት ቦታ አይደለም። ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ስትገቢ ልትማሪ ነው የገባሽው እንጂ በፍቅር ስም አስቀያሚና ህይወትሽን የሚያበላሹ ነገሮችን ሰርተሽ ፀፀት ይዘሽ ልትወጪ አይደለም። ግቢው ውስጥ ፍቅር የሚባል ጨዋታ አይሰራም። ግቢ ውስጥ ያገኘሽው ፍቅር ልክ ተመርቀሽ ስትወጪ ይዘሽው የምትወጪው አስቀያሚ ጠባሳ ነው። ዩኒ ውስጥ ተፋቀርን ያሉ ጥንዶች በአመዛኙ የፍቅር ህይወታቸው እዚያው አብቅቶ ነው የሚወጡት። ራስሽን በፍቅር አታለሽ አላማሽን እንዳትስቺ! ስለዚህ No to LOVE! ምክር ቁጥር ሶስት: ከቤተሰብ ሳለሽ ያልጀመርሽውን ሱሳሱስ መጀመር የለብሽም። በጥናት ስም ቡና መጠጣት ከጀመርሽ ወደ ጫት ይቀጥላል። በጭንቀት ስም ጫት ከጀመርሽ ወደ ሲጋራ ያድጋል፤ ወደ አስካሪ መጠጥ፣ ወደ ክለቦችና ዝሙት እያዘገመ ይወስድሻል። መጨረሻው ራስን ማጥፋት ሆኖ ያርፈዋል። ስለዚህ No to ADDICTIONS! ምክር ቁጥር አራት: በጣም ወሳኙ ምክሬ ነው። ጓደኛ ምረጪ! የሰው ልጅ በህይወት ሲኖር ከቤተሰቡ ያልሆነ ቢያንስ አንድ ጓደኛ ይኖረዋል። ይህ ጓደኛሽ ሁሉ ነገርሽን የሚወስን ጓደኛሽ ነው። "ጓደኛህን ንገረኝ ማንነትህን እነግርሃለሁ" ነው የሚለው ተረቱ። ከላይ የጠቀስኩልሽ ሁለቱ ምክሮችም በጓደኛ ግፊት የመከሰት እድላቸው በጣ.....ም ሰፊ ነው። ጓደኛው ትንሽ የሆነ ሰው፣ ትንሽም ሆኖ ጥሩ የሆነ ጓደኛ ያለው ሰው ለደስታም ለስኬትም የቀረበ ነው። የኔን ምሳሌ ብሰጥሽ እንደ እድል ሆኖ ከአራት የሚበልጡ ከተሞች ላይ ኖሬያለሁ። በያንዳንዱ ከተማ ላይ ከሁለት የማይበልጡ ወዳጅ ጓደኞች አሉኝ። እነዚህ ጓዶቼ ወይ በእውቀት፣ በስነምግባር፣ በገንዘብ፣ በእድሜ የሚበልጡኝ/የምበልጣቸው ናቸው። ወደነዚያ ከተሞች ስሄድ አልቸገርም ከነርሱ ውዬ፣ ስራዬን ሰርቼ፣ ተዝናንቼ እመለሳለሁ። ሲቸግረኝና ሲከፋኝ ከጎኔ ናቸው። እነርሱም ሲቸግራቸውና ሲከፋቸው ከጎናቸው ነኝ። ሀይማኖት ቢለየን እንኳ በጣም የተቀራረብን ነን። በጓደኛ ማግኘት ያለብኝን ደስታ ከነርሱ ስላገኘሁ ብዙ ጊዜ ደስተኛ ነኝ። ስኬት ብለን ላሰብነው አላማችንም አብረን እየተጓዝን ነው። ደስ የሚለው እንዲህ ሲሆን ነው። ለጥሩ ነገር የሚገፋፉ ጓደኞችን ብቻ ተጎዳኚ። ስለዚህ No to BAD FRIENDS & PEER PRESSURE! የቀረ ነገር ካለ ሌሎች ይጨምሩልሽ። መልካም ህይወት!
Feb 14, 2023