Guys 12 this year mnftnew nhase west nw ytbalew ewnet nw ?,2015 mnftnew malet nw?😳
Feb 11, 2023#MoE ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች ያረጋገጠውና ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተላከ አንድ ደብዳቤ ፦ - የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ነሐሴ አጋማሽ በከፍተኛ ተምህርት ተቋማት ውስጥ ለመስጠት ታቅዷል። - የ2015 ዓ/ም የመጀመሪያ ዲግሪ የተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና እስከ ሐምሌ 15 /2015 እንዲጠናቀቅ ታሳስቢ ተደርጓል። - የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው በመንግስት የኒቨርስቲዎችና ተቋማት የሚደለደሉትንና በራሳቸው ወጪ በመሸፈን በግል የሬሚዲያል ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎችን በተመለከተ ፦ • የራሚዲያል ፕሮግራም ለአራት (4) ወራት ከየካቲት 15 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ሰኔ 15 ቀን 2015 ዓ.ም እንዲሰጥ ታቅዷል። • የሬሚዲያል ፕሮግራም በተፈጥሮ ሳይንስና ማህበራዊ ሳይንስ በሁለት መስክ ተከፍሎ ከማዕከል በተዘጋጀ ይዘት መሰረት ዩኒቨርስቲዎች ተጨማሪ የሚያክሉትን በማካተት በተዘጋጀው መነሻ መሰረት ፕሮግራሙ እንዲከናወን ታቅዷል። • የሬሚዲያል ፕሮግራሙ ተጠቃሚ ተማሪዎች ተከታታይ ምዘና እንዲኖራቸው ተደርጎ በየተቋማት የሚሰጠው ምዘና 30 % እና በማዕከል የሚዘጋጀው ፈተና 70% ተመዝነ በድምሩ አማካይና ከዚያ በላይ (50 ከመቶና በላይ) የሚያመጡት በመንግስት ተቋማት ሲከታተሉ የቆዩት በዚያው ተቋም መቀጠል የሚችሉ ሲሆን በራሳቸው ወጪ ሸፍነው ወደ ግል ተቋማት ሄደው መማር ቢፈልጉ መብታቸው የተጠበቀ ይሆናል። Approved by tikvah ayzosh atedenagechi gize alesh (ተጨማሪውን ከደብዳቤው ያንብቡ) @tikvahethiopia
Feb 11, 2023