ከቅዱስ ሲኖዶሱ የሚወጡ መግለጫዎች፣ ማብራርያዎች እና ማሳሰቢያዎች የያዟቸው የአገላለፅ ጥበቦች እና የአቀራረብ ስርዐቶች በትልልቅ የህዝብ ተግባቦት (Public Relations/Communications) ተቋማት እንኳን በብዛት የሚታይ አይደለም። ምናለ የፖለቲካ አመራሩም እንዲህ ሰከን ያለ፣ በእውቀት የታጀበ እና ስርዐትን የያዘ የኮሚኒኬሽን አሰራር ቢኖረው ብዬ ተመኘሁ። Mn tlalachu ezi ngr lay??
Feb 10, 2023እንደ አጠቃላይ ስናየው የጽሑፍ አቀራረብ እና አገላለጹ rhetoricን የጠበቀ ነው የሚያስብል እና ብዙ ሰዎች ወደ ራሱ እንዲስብ የሚያደርግ ዓይነት ቢሆንም ሰከን ያለ ነው የሚለው ግን አሳማኝ ሆኖ አይታየኝም። መስከኑ የሚመሰከረው ከዛ በኋላ በሚመጣው feedback እና የመልስ ምቶቹ እጻጻፍ ላይ እንደመሆኑ ብዛ በኩል የምናየው ከሆነ ሰፊውን ህዝብ ለአመጻ የሚያዘጋጅ ዓይነት ነው። በሃይማኖታዊው ጎን ካየነው..... ከግብጽ ሲኖዶስ ጋር ስናነጻጽረው በጥበብ እና በእውቀተ ሀይማኖት የቀና ነው ለማለት አያስደፍርም። ምክንያቱም በቤተክርስቲያን ቀኖና መሠረት መግለጫ(magazine) እንዴት ይቀርባል፣ ማን ይቀርባል የሚለውን የጠበቀ አይደለም። ግን መካድ የማይቻለው ነገር አጻጻፉ ትልቅ rhetoric ያለው እና influential የሚያደርግ ፍልስፍናን የተጠቀሙበት ነው።
Feb 11, 2023