ተስፋ የሚያስቆርጣችሁ ነገር አጋጥሟቹ ያቃል እን ? በአንድ ቀን የያዛቹት ከእጃችሁ ሲጠፍ ምንም ተስፋ የምታረጉበት ነገር ሳይኖር ሲቀር ...እንደዚህ አይነት ነገር ሲፈጠር ምን ታደርጋላችሁ
Feb 06, 2023ፈጣሪህን አመስግነህ ሌላ ተስፋ መሰነቅ ያ አኺ ህይወት ፈተና ናት። ጥሩ ነገር እንደምታስበው መጥፎ ነገርም አስብ። ይህን ማድረግህ ውስጥህን ለሁሉም ነገር ያዘጋጀዋል። አንድ ወዳጅ ቢኖርህ "ነገ ጠላቴ ሊሆን ይችላል" ብለህ ካላሰብክ የሆነ ጊዜ ላይ ወዳጅህ ተቀያይሮ ጠላትህ ሲሆን ትሰበራለህ። ምሳሌ ነው የሰጠሁህ። እህት ነበረችኝ በካንሰር ህመም ተሰቃይታ አርፋለች። ከታመመች በኋላ ትድናለች ብዬ ተስፋ አደርግ ነበር። እንደምትሞት ማሰብ እንኳ አልፈልግም ነበር። አላህ ወስኖ ሲወስዳት በቤተሰብ ደረጃ ነበር ስብርብር ያልነው። ሞቷን አልጠበቅንም ነበር። እና እኔ ትምህርት ወስጃለሁ። "እናቴም፣ አባቴም፣ እህት ወንድሞቼም ሞተው ብቻየን ልቀር እችላለሁ፤ ለሁሉም ልዘጋጅ!" እያልኩ ራሴን አስጠነቅቃለሁ። "የመኪና አደጋ ደርሶብኝ እግሮቼን ላጣ እችላለሁ" እያልኩ ራሴን አዘጋጃለሁ። ካለፈው ትምህርት ወስጃለኋ። አንተም ከዚህ ትምህርት ወስደህ ሌላ ብሩህ ተስፋ ሰንቀህ ለመጥፎዎቹ ጊዜያት ተዘጋጅተህ እስከተፈቀደልህ ጊዜ ኑር።
Feb 07, 2023