ሰላም እንዴት ናችሁ🙌 ዕድሜዬ 25 ነው ኢንጂነር ነኝ ከሀገር ውጪ ስራ አጊኝቼ process እየጨረስኩ ነው። በሚገርም ሁኔታ ለረጅም አመት ከኖርኩበት የፍቅር ህይወት ወጥቼ ህይወትን ብቻዬን መምራት ከጀመርኩ 1አመት ሆኖኛል literally ብቻዬን እና ረጅም ጊዜዬን በማንበብና ራሴን በማጎልበት ዙሪያ እያሳለፍኩ እዚህ ደረስኩ። ባለፈው ሳምንት ልደቴ ነበር እና ከዚህ በፊት ከነበሩት የልደት ቀኖቼ በሙሉ የተለየ ነበር ከወንድሞቼ ውጪ መልካም ልደት ያለኝ ሰው አልነበረም ከዚህ በፊት ያው ፍቅረኛም ስለነበረኝ ሌሎች ብዙ ጓደኞችም ስለነበሩኝ በጣም ቀውጢ ቀን ነበር ሚሆነው የፍቅር ህይወቴ ሲበላሽ ሁሉን ተውኩት ከዛ ጊዜ ጀምሮ ምን ያህል ራሴን ለማበርታት የሄድኩበት መንገድ ብቸኛ እንዳደረገኝ ተረዳሁ Telegram ላይ last seen ነኝ facebookም ላይ active አይደለሁም አስፈላጊ መልዕክት ካልሆነ አልመልስም ይህ ሁሉ ለካ ከሰው አርቆኛል። ጥያቄዬ ታዲያ ግማሹ ስሜቴ ትክክል እንደሆንኩ እና በዚሁ እስከህልሜ መጓዝ እንዳለብኝ ይነግረኛል ግማሹ ደሞ ስህተት እንደሆንኩ ይነግረኛል ከልደት ቀኔ በኋላ ማለቴ ነው እና ምን ትመክሩኛላችሁ?
Feb 06, 2023ምንም አዲስ ነገር የለውም። አንድ አይነት ህይወት እየመራን ነው። ጥቂት የልብ እና የችግር ጊዜ ወዳጆች ካሉህ፣ ቤተሰብ ከጎንህ ከሆነ፣ ያንተ ያልሆነችን ሴት ከማባረርና ባሪያዋ ከመሆን ራስህን ነጻ ካወጣህ (የራሴ የምትላት ባለቤት ካለችህ)፣ የራስህ ስራ ካለህ፣ ጤነኛ ሆነህ መኖር ከቻልክ ምንም አያስፈልግህም። ጥቁር መነጽርህን አድርገህ😎 ከወንድሞችህ ና ጥቂት ጓዶችህ ጋር ሁነህ ፈታ በል🏖🏝 ሐቪቪ ፈታ በል 🤦🏽♂
Feb 07, 2023