ሰላም ✌️ የ 10ኛ ክፍል ተማሪ ነኝ ነገር ግን አንድ ነገር አለ ከአባቴ ጋር መስማማት አልቻልኩም ከሱ ጋር መግባባት ካቃተኝ almost 3 አመታት ተቆጥረዋል እና ምን ማድረግ አለብኝ ብላቹ ታስባላቹ እሱ ጭራሽ ከኔ ተቃራኒ ሰው ነው ምናልባትም ከኔ ሊሆን ይችላል ችግሩ እስቲ ምን ትመክሩኛላችሁ 😔
Feb 06, 2023በህይወት ውስጥ ሁለት ነገሮች አሉ መቀበል እና መቀየር ምንላቸው መቀበል ስንል የተፈጠርንበትን ሀገር፣ቤተሰብ እንዲሁም የእኛነታችን መገለጫ የሆኑትን አካሎቻችንን መቀበል እንጂ መቀየር አንችልም መቀየር ማንችለውን እንቀበለዋለን በእርግጥ ባንቺ ጫማ መቆም አልችልም ግን ያው ቤተሰብ ብዙ ጊዜ አስቸጋሪ ናቸው የአስተሳሰብ ልዩነት ስላለን እና አሁን ባለሽበት ሁኔታ እራስሽን መቀየር አባትሽን መቀበል ሳይኖርብሽ አይቀርም አንዳንዴ ሁኔታው ጥሩ ወይም መጥፎ ሚሆነው በአስተሳሰባችን ልኬት ነው እና የአባትሽን ድርጊት ጥሩ ወይም መጥፎ ፤ ተቃራኒ ወይም ተመሳሳይ ከሚለው ፅንፍ አውጥተሽ ለመረዳት ሞክሪ።
Feb 07, 2023