Ebakachu be kenanet melesulgn ahun be betechrstianachn mndnw eyetefere yalew erasun be rasu sindos yarege abat wede atonet medregachew endeweredum semechalew aweqalew gn sele teqlay ministru ena selelochm negeroch sefa yale mebrarya setugn ebakachu
Feb 05, 2023አብራሩልኝ* ስለተባለ ጽሁፉ ረዝማል። የእኛ ቤተክርስቲያን አስቀድማ ከሾመቻቸው ፓፓሳት መካከል ሶስቱ በሌላቸው ስልጣን እና የሰይጣን ሀሳብ ሌሎች የማይታወቁ ከ20 በላይ የሆኑ ሰዎችን እንደ ፓፓስ አድርገው መሾማቸው አሁን ላለንበት ሁኔታ አንድ መነሻ ነው።ሲኖዶስ ማለት የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓፓሳት እና እንድ ፓትሪያርክ ኮሚቴ እንደማለት ነው በቀላል አማርኛ።ሁሌም ሲሰበሰቡ አንድ ክፍት ወንበር በመሀላቸው አለ እርሱም የ መንፈስቅዱስ ነው የሚወሰነው ምክክር ሁሉ ውስጥ እግዚያብሔር አለ ማለት ነው።እነዚህ አባላት ሚመረጡበት ከ ቅዱሳን ሐዋርያት ጀምሮ የመጣ ስርአት አለ።ፓፓስ መሾም ማፅደቅ የሚችለው ፓትርያርኩ ብቻ ናቸው።ለሁሉም የስልጣን ተዋረድ አለው። እንዜ ወንበዴዎች እንደ ሽፋን ይዘውት የመጡት ነጥብ በኦሮሚኛ ቋንቋ እንገልገል የሚል ነው።ይህም አይምሮ ላለው ሰው ሁሉ ልክ የሆነ ጥያቄ ነው።ግን ከድሮ ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል አገልግሎት እየተሰጠ ያለው በኦሮሚኛ ቋንቋ ነው እንደ ተለይቶ በኦሮሚያ ክልል ብቻ ነው ቅዳሴ በራሳቸው ቋንቋ የሚቀደሰው።ሌሎቻችን ጋር በግዕዝ ቋንቋ ነው።መፅሐፍ ቅዱስን ጨምሮ ሌሎች መንፈሳዊ መፅሐፍት እንዲሁም መዝሙራት በኦሮሚኛ በሽ ናቸው። ይህ የወንበዴዎቹን አላማ ፍንትው አድርጎ ያሳያል።እሺ ያሉት እንኳን ልክ ቢሆን የሄዱበትን መንገድ እግዚያብሔር ሊቀበለው ይችላልን?የትኛው የእግዚያብሔር ሰው ነው ለእግዚያብሔር ልጆች አስቦ ቤቱን ሚበጠብጠው በወታደር ሚታጀበው?ጥያቄውን በፀሎት እና በሱባኤ በእንባ መጠየቅ ማሳወቅ ማስተማር መምከር ይበጃል ወይስ በሀይማኖት ቤት ጉልበተኛ መሆን? ከዚህ ጀርባ ማን እንዳለ ለመመልከት ለነዚህ ወንበዴዎች ከለላ እና ድጋፍ ማን እያደረገ እንደሆነ ማየት በቂ ነው።ከዚህ በፊት በእኛ አማኞች ላይ የመግደል የማፈናቀል ስራን ከሌላው ጊዜ በጣም በጨመረ መንገድ እያካሄደ ያለው የብልግና መንግስት ነው።ይህንን የሚያደረገው ለምን ነው ቢባል በእነሱ ጭንቅላት እምነት ኦርቶዶክስ ናት የኢትዮጵያ መሰረት ይህችን ቤት ካፈረስን ሌላው አይከብደንም የሚል ነው።ለምሳሌ እነዚህ ወንበዴዎች ያሰቡት ቢሳካ ሳይቆዩ የሰርአተ ኦርቶዶክስን አልተመቸንም ብለው ይቀይራሉ።ቀስ በቀስ አማኞችን ከዚህ ቤት ያስወጣሉ።እረኛ የሌለው በግ የተመኘው ሁሉ ይሰርቀዋል።ቀጥለው ወደ አጎራባች ክልል ይዘልቃሉ ልክ አሁን በፓለቲካው እያረጉት እንዳሉት። ልክ እንደ ዮናታን ያሉ ደግሞ ይሄን አጋጣሚ ይጠቀሙበታል።ለሰው አስበው ቢሆን መልካም ነበር ግን ለአብይ አላማ ብለው ነው።እንደ ትክክለኛ የእምነት መምህር ነኝ ባይ እንደ ዮናታን የመሳሰሉ ሰዎች እንደሚወርዱበት መርከስ ሊወርድ ይችላልን?ያለፈው እንዳለ ሆኖ ሰሞኑን ትንቢት አየሁ ብሎ ሲሳለቅ አብረውት ያሉትን ሲያስጮህ አይተናል።ውሾች ቤታችንን ከበዋታል*እስቲ ከጊዜ በዃላ እንደ በድን ለሚከተሉት ነፍሳት ምን ብሉ ሊያስተባብል እናያለን። አብይ በንግግሩ/በጽሑፍ ላይ የተጠቀማቸው ቃላት/አባባሎች በሙሉ ልክ አይደለም።ድርድር* የሚደረገው እኩል አቅም ስልጣን ባላቸው አካላት መካከል እንጂ በሌባ እና በተሰረቀበት አካል መካከል አይደለም።ሁለቱም ጋር እውነት አለ* ማለት ሌባው እውነትን ይዞ ነው የሰረቀው እንደማለት ነው።ምንም እውነት የላቸውም።ለቤተክርስቲያን ቦታ ከሌላው በላይ ሰተናል* ያለው ሙሉ ውሸት ነው የነበረንን ወሰደ እንጂ ከራሱ ቆርሶ ምንም አልሰጠንም።የመንግስት አካል ጣልቃ አይግባ* ማለት ህግ አታስከብሩ ማለት ነው። ስለዚህ አሁን በቤታችን እይተፈጠረ ያለው ከብዙ በጥቂቱ ይህ ነው።
Feb 06, 2023