20 amete nw ,abaten betam asazignewalhu ,endazenebignm yitawekegnal,mawerat kakomn almost 1 year eyetetga nw ,yebetu yemejemria lij ene negn,yetetalanibet mkinyatm ,tmhrten ke regular wede weekend slazorkut nw ahun gn ,esun lemasdeset sil regular memar lijemer nw , Ena yikirta liteyikew ena wedekedmoachn enimeles weys zm biye eskemimar dres litebik,(smetun takutalachu mechem kebeteseb gar tseb lezawm and bet eyenoru) ena please hasabachun share argugn?
Feb 05, 2023እኔ 30 አመቴ ነዉ። አባቴ ሀይለኛ የሚለዉ ቃል አይገልፀዉም። ከህፃንነቴ ጀምሮ ምንም መሳሳትም መናገርም አልችልም ይደበድበኛል። ስንዘጋጋ ቤት ሰላም ይሆናል። ማናገር ስጀምር እያንዳንዱ እንቅስቃሴዬ ለሱ ስህተት ነዉ። ምንም ነገር ላረግ ሳስብ አይምሮዬ ቆይ ይለኛል የሱን ፍራቻ ያስባል። በህይወቴ ብሳሳት አለም እንደምትዞርብኝ እያሰብኩ ነዉ ያደኩት። ወንድ ባጠገቤ ካለፈ ልቤ ቀጥ ነዉ የሚለዉ። 19 ዓመቴ አካባቢ እንደዘጋሁት ተነጋግረን አናቅም። አባት ለሴት ልጅ ከለላዋ ነዉ። ከሱ ጋር ከተዘጋጋን በኋላ ዓለምን ለብቻዬ እንደምጋፈጣት ነዉ የማዉቀዉ😢😢 ወንድ መቅረብ እና ባል የማግባትም ፍላጎት የለኝም። እሱ አዝኖብኝ ከሆነ በቀጣይ ህይወቴ እፈተናለሁ ብዬ አስባለሁ። ይቅርታ ካልኩት ቤታችን በኔ ስበብ ይናጋል። ይቅርታ የሚለዉ ቃል ከአፌ መዉጣት አይችልም አሁን ላይ አባቴን በጣም ተቀይሜዋለሁ😭😭 ሁሉም ወላጅን አታሳዝኑ ይላል እንጂ ልጅን አታሳዝኑ አይልም። እኔ ግን ልቤ ድንጋይ ሆኗል። ይቅርታ አልልም! አንቺ ግን ቢያንስ ይቅርታ የማለት እድል አለሽ ይቅርታ በይ አባትሽን በጊዜ እንደ እኔ ጊዜዉ ሳይረፍድ። ቢያንስ አባትሽ ላንቺ አዝኖ ነዉ የተጣላሽ።
Feb 06, 2023