ሰላም ምን መሰላቹ በጣም የቅርብ ጓደኛ አለኝ በቃ በጣም ምንዋደድ ምንተሳሰብ ሁሉም ነገሬ የሆነ የህይወቴ አንድ አካል የምለዉ እሱም እንደዛ የሆንኩለት ከጓደኛም በላይ ነን ከህይወቴ ላወጣዉ ማልችለዉ ሰዉ ነው ከሱ መለየት መራቅ አልችልም እሱም እንደዛዉ ንፁ ጓደኝነት ብቻ ነዉ መሃላችን ያለዉ እና ሰሞኑን ሴት ጓደኞቼ ከሱ ጋር ያለሽን ነገር ቀንሺ ወይ አቁሚ እያሉኝ ነው እንዲህ ሆኜ የፍቅር አጋር ማግኘት እንደማልችል በፍቅር ግንኙነት ዉስጥ ወንድ ጓደኛ እንደማያስፈልግ ይነግሩኛል እርግጥ ነው አሁን ላይ ፍቅረኛ የለኝም ግን ለወደፊት ህይወቴ ያሰጋል ትላላቹ መለያየት አይታሰብም ለምርጫ ማቀርበዉ ሰዉ አደለም ምን ባረግ ነው አብሬ ማስኬድ ምችለዉ
Feb 03, 2023POV : እንዴ sis ውስጥሽ ከፈቀደ እሱም ስሜት ካለው ከሱ ጋር ለምን አትሆኚም ሌላ R/ship ከምትጀምሪ ይህን ልጅ አጥብቀሽ ያዢው ።
Feb 04, 2023