ሰላም እዴት ናቹሁ 12 ተፈኘ ውጤት መቶልኛል ግን ግቢ ለመግባት ግራ ተጋባሁ ምን መሰላቹሁ ቤተሰብ እኔን ለማስተማር አቅም የላቸውም የው ደሞ ግቢ ለመሄድ የተለያዩ ወጪ አሉ የቦርሳ የትራንስቦርት ምናምን ፡፡ ግቢ ለመግባት ያለውን ነገር ፈላልጌ ልሄድ እችላለሁ ግን እዛ ከሄድኩ በኀላ ብር ለአንዳንድ ነገር ያስፈልጋል እኔን የሚረዳኝ ቤተሰብም ሆነ ዘመድ የለኝም ፡፡ ምን ባረግ ይሻለኛል ? እደኔ ሆናቹሁ የገባቹሁ ካላቹሁ እዴት አርጋቹሁ ተመርቃቹሁ ወጣቹሁ ፡፡ ለትብብራቹሁ አመሰግናለሁ
Feb 01, 2023እንዳንተ በባዶው ነው የገባሁት። የትራንስፖርት እንኳን ከሰው ተበድሬ ነው የሔድኩት። ግቢ ከገባሁ በኋላ የምግብ፣ የማደሪያ አያሳስብም። ሌሎች አንዳንድ ወጭዎችን የሸፈንኩት ማታ ማታ እየሠራሁ ነው። እሑድ ቅዳሜ እንዲሁም ማታ ብዙ ሥራዎችን እሰራ ነበር። ሦስተኛ ዓመት ስደርስ ብዙ ሰዎችን ተዋወቅሁ። አንዳንድ ሥራዎችን ሰጡኝ። የወረቀት ሥራዎች ሲሆኑልኝ ቀለለልኝ። አሁን ተመርቄ አንድ የግል ድርጅት ውስጥ ጥሩ ደመወዝ እየተከፈለኝ መሥራት ከጀመርኩ አንድ ወር ሆነኝ። በርታ! እንዳትቀር።
Feb 01, 2023