ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ኃጢአትና ስድብ ሁሉ ለሰዎች ይሰረይላቸዋል፥ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ለሰደበ አይሰረይለትም። #በሰው_ልጅ ላይ ቃል የሚናገር ሁሉ ይሰረይለታል፤ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ግን የሚናገር ሁሉ በዚህ ዓለም ቢሆን ወይም በሚመጣው አይሰረይለትም።(የማቴውስ ወንጌል12፥32-33) ይህ አንቀፅ እንደሚነግረን "መንፈስ ቅዱስን" የሚሳደብ ይቅር አይባልለትም አየሱስን(የሰው ልጅን) የተናገረ ይሰረይለታል። ለምን? ኢየሱስ ከመንፈስ ቅዱስ በምን ያንሳል? መንፈስ ቅዱስ ከኢየሱስ እንደሚበልጥ እና እኩል እንዳልሆኑ አያመላክትም?
Jan 29, 2023ኢየሱስ ክርስቶስን ራሱ "የሰው ልጅ" ማለት ራሱ መንፈስ ቅዱስን መሳደብ ነው። አባ ሕርያቆስ እንዳለው አብ ያስባል ወልፍ ይናገራል መንፈስ ቅዱስ ያከናውናል። መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ድንግል ትጸንሳለች ሲል በአብ ልብ ታሰበ ቃለ ወልድ አደረ መንፈስ ቅዱስ መሰከረ። ጌታችንን የሚሳደቡት ሰዎች እሱ ማን እንደሆነ ስላልገባቸው እና እንደነሱ የሰው ልጅ ብቻ ስለመሰላቸው ነው፥ ቢያውቁ ኑሮ ባልተሳደቡ ነበር። ቢሳድርቡ ግን አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስን እንደተሳደቡ ነው።
Jan 29, 2023