እኔ ምለው ፈጣሪ ለመኖሩ ተፈጥሮ መልስ ትሰጡናላችሁ እኔ ግን ያልገባኝ እኛ አለን ወይ ነው በተለይ ፈጣሪ ሁሉንም አዋቂ ነው ካልን ገና ከመፈጠራችን አንስቶ እስከ ሞታችን ያለውን ሙሉ ታሪካችንን የሚያቅ ከሆነ እኔ የማላውቀው ነገየን ሁሉ የሚቅ ከሆነ እኔ አለው ወይ ነው ጥያቄዬ? በቃ እኮ ይህ ማለት እኛ የፈጣሪ ድርሰቶች ነን የተሰጠንን ካራክተር በሚገባ የምንተውን ምርጥ አክተሮች እና አሁን ራሱ ይህን እኔ ፅፌዋለው አይመስለኝም ምከንያት ገና ሳልፈጠር ፈጣሪ ይህን ቀዚህ ሰአት እንድፅፍ ያቅ ነበራ
Jan 25, 2023አንድ ሰው ህንፃ ላይ ቆሞ ሁለት ከተቃራኒ አቅጣጫ በእኩል ፍጥነት እየመጡ ያሉ መኪኖችን ቢመለከትና በርገጥኝነት ሁለቱ መኪኖች ኩርባው ላይ ሲገናኙ እንደሚጋጩ ቢያውቅ በመጋጨታቸው ላይ የሰውየው እጅ አለበት ያስበለዋል?...በፍፁም! የፈጣሪም ነገር እንዲሁ ነው።ማወቅ እና መወሰን ይለያያል።በአምላክነቱ ሁሉን ያውቃል ማለት ሁሉን ወስኖ ፅፎና አስፍሮ አስቀምጦታል ማለት አይደለም።ሲጀመርም ይህን ባያውቅ ነበር አመላክ መሆኑ የሚያጠራጥረኝ!
Jan 26, 2023