ሰላም ሰዎች የሶስተኛ አመት university ተማሪ ነኝ እና ትምህርት በጣም ነው የሰለቸኝ እና ምን እንደሆንኩ ሳላውቅ በጣም ድብርት ውስጥ እገባለሁ ሲደብረኝ ደሞ ሰው ሁሉ እስኪያስጠላኝ ነው የሚደብረኝ እና ደሞ በእያንዳንዱ ውሳኔዎቼ ካደረኩት በኋላ በጣም እናደዳለሁ ምን ትመክሩኛላችሁ አመሰግናለሁ
Jan 25, 2023ሰላም እንዴት ነህ; ድብርት ከባድ ህመም መሆኑን እረዳለሁ፡፡ ብዙ ጊዜ እኔም ደብሮኝ እና ልክ እንዳንተ ዓይነት ስሜት ተሰምቶኝ ስለሚያዉቅ፡፡ አይዞህ እሺ ሁሉም ይስተካከላል፡፡ እንደ ምክር የምነግርህ ግን ዉስጥህ ያለዉን ስሜት አዉጥተህ ለመናገር ሞክር ፣ በዉስጥህ ምንም ነገር አትያዝ ፣ ነገሮችን በዉስጥህ ላንተ ብቻ የምትይዛቸዉ ከሆነ ብዙ ጊዜ ደጋግመህ እንድታስባቸዉ እና የበለጠ ድብርት ዉስጥ እንድትገባ ነዉ የሚያደርግህ ስለዚህ ሀሳቦችህን ተናገራቸዉ የሚሰማህ ሰዉ ከሌለ ደግሞ ጻፋቸዉ እና እንደ ሀይማኖትህ ወደ ጸሎት ቦታዎች ሂድና ከአምላክህ ጋር አዉራበት፣ እመነኝ ይሻሻላል ካልሆነ ግን የህክምና ባለሙያ ታናግርበታለህ እሺ፡፡ በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ፣ ብቻህን አይደለህም ብዙዎች በዚህ መንገድ አልፈዋል እያለፉም ነዉ፣ እንዳንተ ግን ስሜታቸዉን አልተናገሩም ስለዚህ ቢያንስ አንድ እርምጃ ቀድመሃቸዋል በዚሁ ቀጥልበት፡፡ ሰዎችን ደግሞ አትግፋ ፣ ልታወራቸዉ ሞክር እባክህ ማዉራት ብዙ ነገር ያስተካክላል እሺ፡፡ ይሄ ሁሉ ሆኖ አልሻሻልም ካለህ እኔ የህክምና ባለሙያ አገናኝሀለዉ፡፡ መልካም ቀን፡፡ ማዉራት ከፈለክ በዉስጥ መስመር ማዉራት እንችላለን፡፡
Jan 26, 2023