ሰላም ቤተሰቦች ሰለ ልማት ባንክ ሰሞኑን ምን እየተሰራ ነው ማለት ምን አዲስ ነገር አለ ሰዎች ሲያወሩ ሰምቼ ነው እስቲ ምታቁ አብራሩልኝ
Jan 25, 2023የስልጠና ፕሮግራም ጥቆማ‼ ===================== ✍ እኔ ሥራ እየሠራ ሌሎችንም የሚያነሳሳ፣ የጋን ውስጥ መብራት ያልሆነ ሰው ይመቸኛል። በሉ! ተመዝገቡና ሰልጥኑ! «የበለጠ እንዲገባን . . . (እባካችሁ የተፃፈ አንብቡ. . . ሊዝ ፋይናንስ ማለት "የካፒታል እቃዎችን ገዝቶ በዱቤ ግዥ ስርአት ለኪራይ የሚቀርብበት አገልግሎት ነው" በአጭሩ"ለስራችሁ የሚያግዛችሁን ማሽን ይገዙላቹሀል" የልማት ባንክ ሊዝ ፋይናንስ ለምን ተመረጠ? 1. ሐቃችን ስለሆነ፣ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ብድር ተቀብሎ ለዜጎች የሚያከፋፍል መሆኑ። 2. ከ2 ሚልዬን እስከ 60 ሚልየን የሚደርስ ማሽን መግዛቱ። ሌሎቹ ከ10 ሚልየን በላይ አይገዙም። 3. ቀጥታ ከአምራች ማሽኑን መግዛቱ ለምሳሌ፦ 10 ሚልዬን ብር የሚያወጣ የዳቦ ማሽን ብትፈልጉ፣ ባንኩ ጥያቄያችሁን ከተቀበለ ማሽኑን የሚገዛላችሁ እዚህ ከሚገኝ አስመጭ ሳይሆን ቱርክ፣ ጣልያን ወይም ቻይና ካለው ዋናው ካምፓኒ ነው። ይህ ደግሞ . . . የአስመጪውን የተጋነነ ትርፍ ስለሚያስቀር በተመጣጣኝ ዋጋ ታገኛላችሁ። 4. በተጨማሪም አስመጪው ማሽኑን ሲያስመጣ በብላክ ሂሳብ ነው ዶላሩን አስቦ የሚሰራው። ልማት ባንክ ግን ቀጥታ ከፋብሪካ ስለሆነ ስሌቱ የሚሰራው ባንክ ላይ በሚውለው ምንዛሬ ዋጋ ነው። ለምሳሌ፦ የ40,000 ዶላር ማሽን ማስመጣት ብትፈልጉ አስመጪው አሁን ባለው የብላክ ዋጋ ነው ሂሳብ የሚያወጣላችሁ። ይህም ማለት 40,000*100= 4,000,000 ብር ልማት ባንክ ግን 40,000* 54=2,160,000 ብር በትንሹ የ40% ልዩነት አለው። ይህ እንግዲህ የአስመጪውን ትርፍና ትራንስፓርት፣ የኮንቴነር ኪራይና ሌሎች ወጪዎችን ሳይጨምር ነው። 5. ከሌሎች ሊዝ ፋይናንስ ከሚሰጡ ተቋማት ጋር ሲነፃፀር የአገልግሎት ክፍያው ዝቅተኛ ነው፣ በአመት 9% ብቻ ነው። 6. መጀመርያ በዝግ አካውንት ያስቀመጣችሁትን 20% ተቀማጭ ማሽኑን በተረከባችሁ ማግስት ለስራ ማስኬጃ መልቀቁ። 7. ስራችሁ ጥሬ እቃ ከውጭ የሚያስመጣ ከሆነ ባንኩ ላይ በምትከፍቱት ተንቀሳቃሽ አካውንት ባስቀመጣችሁት የገንዘብ መጠን ልክ የውጭ ምንዛሬ(ዶላር) መፍቀዱ/መስጠቱ👍 8. ከወለድ ነፃ አሰራር ለመጀመር ጫፍ ላይ መሆኑ ሌላም፣ ሌላ . . . ልብ በሉ‼ እየዘረዘርኩ ያለሁት የባንኩን አሰራር እንጂ ሸሪአዊ ብያኔ አይደለም። ይህን እድል ከሸሪአው ጋር አጋብቶ ጥቅም ላይ በማዋሉ ረገድ የሁላችንም ተሳትፎ ይሻል። መጀመርያ ተመዝገቡ፣ ሰልጥኑ እድሉ አያምልጣችሁ። ሌላውን ከስልጠና ቡሀላ እንመለስበታለን።» ለምታውቋቸውም ንገሯቸውና ይሰልጥኑ። ምዝገባው ከጥር 06–16, 2015 ነው። ስለ ልማት ባንክ የተነሱ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች፦ ለመመመዝገብ ምን ያስፈልጋል? መታወቂያ/ፓስፓርት/መንጃ ፈቃድና የት/ት ማስረጃ(10 ወይም 12ኛ ክፍል/ ከዛ በላይ ለመመዝገብ ንግድ ፈቃድ ያስፈልጋል? የት/ት ማስረጃ ለሌላቸው ብቻ ነው የሚያስፈልገው ተፈላጊ የት/ት ደረጃ ላለቸው አያስፈልግም። ምዝገባው መች ነው? ከጥር 06-16 ይቆያል የት ነው ምዝገባው? አቅራቢያችሁ ላይ የሚገኝ ልማት ባንክ ቢሮ ሰው ሊመዘገብልን ይችላል? ህጋዊ ውክልና ካለው ብቻ ነው የሚቻለው ስልጠናው መች ነው የሚጀምረው? ከጥር 22-26፣ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ይቆያል። ስልጠናው የት ነው የሚሰጠው? በተመዘገባችሁበት ከተማ/ አቅራቢያ ቦታ/ ክፍያ አለው? በነፃ ነው ምንም ክፍያ የለውም፣ ወጪው ሙሉ በሙሉ በባንኩ ነው የሚሸፈነው። የመንግስት ሰራተኛ መሰልጠን ይችላል? አዎ፣ ግን ለአምስት ቀን ረፍት መውሰድ አለበት። ስልጠናውን ለመውሰድ በጥቃቅን መደራጀት ግዴታ ነውን? አይደለም፣ ስልጠናውን በግል፣ በድርጅትና በኢንተርፕራይዝ መውሰድ ይቻላል። ስልጠናውን በመውሰዴ ምን ይጠቅመኛል? የልማት ባንክ አገልግሎት ለማግኘት የስልጠናው ሰርተፍኬት እንደ ቅድመ ሁኔታ ይፈለጋል።
Jan 26, 2023