የባለፉት ጥያቄዎች ላይ እንደገልጽኩት በዚህ ጉዳይ ላይ ጽንፍ ይዤ መከራከር አልፈልግም። ግን ድፍረት አይሁንብኝና በጣት ከሚቆጠሩ አበው ጳጳሳት በስተቀር በመላው ሲኖዶስ አባላት ላይ የራሴ ቅራኔ አለኝ። ጳጳሳት ሁሉም መነኮሳት ናቸው፥ መነኮሳት ገዳማውያን እንጂ ዓለማውያን አይደሉም። መነኩሴ ከመነኮሰ በኋላ ብሔርም ሀገርም ዘርም ቀለምም የለውም። ነገደ ገዳማውያን ዘራቸው ሰማያውያን ናቸው። ጦርነት፣ የፖለቲካ ሽኩቻ፣ የቋንቋ ጉዳይ፣ የሀገር ታሪክና የመሳሰሉት በተነሳ ቁጥር በስመ አበው መሰደብ እና መሸማቀቅ በእውነት ስልችት ይላል። የጠቅላይ ቤተክህነቱ ሊቀጳጳስም ቢሆኑ ቅር ያለኝ ነገር አለ። ከዚ በፊት በEthnic affairs ላይ ይናገሩ ነበር። ሌሎች ጳጳሳት ደሞ ይባስ ትግራይ አህጉረስብከት ላይ ጦርነት ያበረታቱ ነበር። አባ ሳዊሮስ ላይ ያለኝ ቅራኔ ደሞ ጵጵስና ምንኩስና እያላቸው ጳጳሳትን በብሔራቸው classify ማድረግ አግባብ አልነበረም።
Jan 25, 2023