ሰላም እንዴት ናችሁ ልጠይቃችሁ የፈለኩት እኔ አሁን በሆነ ቢሮ ተ1ጥሬ ነው ምሰራው በስራዬም አነስተኛ ደሞዝ ነው ሚከፈለኝ ነገር ግን ያው ቤተሰብ ማገዝ ግድ ይለኛል ስለዚህ ከቢሮ ስራ በተጨማሪ ሌላ ስራ ማገኝበት መንገድ ካለ ሀሳባችሁን ብታካፍሉኝ ነው በኮምፒዩተር ዘርፍ ነው የተመረኩት ማስተማር በጣም ነው ምወደው ከኮምፒዪተር ጋር የተያያዙ ጥገናና ማንኛውንም ስራዎች እሰራለው ኔትዎርክ ዝርጋታ መስራት እችላለሁ ፎቶ ሾፕና አንዳንድ ቪዲዮ ኤዲቲንግ ነገርም ሞክራለው ኮምፒዩተር ታይፒንግና ሪራይቲንግም መስራት እችላለሁ ግን ለተጨማሪ ስራ በኦንላይንም ሆነ በሌላም መንገድ የሞከርኳቸው ምንም ሊሳኩልኝ አልቻሉም upwork ላይም ስራዎችን ተቀብዬ ካጠናከኩ በኋላ scam መሆናቸውን ነው ያወኩት ስለዚህ በተለየ መንገድ ስራን እንዴት ልሰራ እችላለው? thanks
Jan 24, 2023አንተ'ኮ ሁሉንም ትጥቅ ያሟላህ ወታደር ነህ። መሳሪያዎችህ ደግሞ ሌሎች ሰዎች በኖረኝ ብለው የተመኟቸው መሳሪያዎች ናቸው።
Jan 25, 2023