Aselamu alykum .... I have lost my father 10 days back ena le teaziya yemimtu sewoch sbr argi yelugnal sbr marg endt endhon gra gebagn yalhonu kalatn alawtam malks becha nw ena yehe sbr matat nw mibalw? ..Betam sbr marg eflgalw gn bka enbayn mkotatr alchalkum
Jan 24, 2023አላህ በመታገስሽ የምትመነጂ ያድርግሽ። አብሽሪ። አባትሽንም ወንጀላቸውን ምሮ የጀነት ወጣት ያድርግልሽ። አንዳንዱ የሚናገረውንም ሲያጣ ዝምብሎ "ሰብር አድርጊ" ይላል። እንደ ባህልም ስለሆነ ብዙ ግድ አይስጥሽ። ነገር ግን ሰው በመጣ ቁጥር የምታለቅሺ ከሆነ ላንቺም ለቤተሰቦሽም ለሟቹም ጥሩ አይሆንም። ራስሽን በሌላ ነገር 'ቢዚ' ለማድረግ ሞክሪ። አለዚያ አትችዪውም። የዛሬ 2 አመት ትንሿ እህቴ ስታርፍ ሀዘኑን መቆጣጠር የቻልኩት ለለቅሶዋ 2 ቀን ሰጥቼ ወደ ትምህርቴ በመመለሴ ነው። አለዚያ ሰዉም መምጣቱን አላቆመም እኔም ማልቀሴን አላቆምም የበር። ሀዘን መጥፎ ነገር ነው። ሰውነትሽን ሰርስሮ የሚጨርስ መርዝ ነው። ሳታረጂ የሚያሸብት ነው። 10 ቀን ሙሉ ቁጭ ብሎ ማልቀስ ከባድ ነው። ተማሪ ከሆንሽ ወደ ትምህርትሽ ሰራተኛም ከሆንሽ ወደ ስራሽ ሂጂ።
Jan 25, 2023