A new muslim here. How do i pray suna salah?The steps please.
Jan 23, 2023በመጀመሪያ እንኳን ደህና መጣህ። አላህ ፈተናዎችን አልፈህ በእምነትህ ጸንተህ ሙስሊም ሆነህ የምትገናኘው ያድርግህ። ወደ ኢስላም ከገባህ ወዲህ ብዙ መሰናክሎች ይጠብቁሃል። ከቤተሰብ ጀምሮ እስከ ሙስሊሙ ኅብረተሰብ የሚጠብቅህ ፈተና አለ። ሁሉንም ታግሰህ በጽናት እለፍ። የዛሬ ሁለት ወር አካባቢ አንዋር መስጂድ ቁጭ ብዬ ሳለ አንድ መልከመልካም ቆንጆ ወጣት መጥቶ ከሰለመ በኋላ የገጠመውን ፈተና ስለራሱ ሲያጫውተኝ በጣም አዝኛለሁ። እንዲሁ አንዲት ሴት ከጴንጤ እምነት ቀይራ በመስለሟ በወጣት እድሜዋ ቤተሰቦቿ ያደረሱባትን መከራ አላህ በአጅር ይቀይርላት የሚያስብሉ ነገሮችን ሰምቻለሁ። ከኛ ከሙስሊሞችም ብዙ የሚጠበቅ ነገር አለ። አላህ ያስተካክለን። ሱና ሰላት ከፈርድ ሰላት የሚለየው ሱና ሰላትን መስገድም አለመስገድም ትችላለህ። ብትሰግድ ጥሩ ነው ትመነዳበታለህ፤ ካልሰገድክም ችግር የለውም። ከፈርድ ሰላት በፊትና በኋላ የሚሰገድ ሱና ሰላት አለ። ከፈጅር በፊት የምትሰገደዋ 2 ረከዓ ሰላት #ምድር_በውስጧ_ከያዘችው_ነገር_ሁሉ_እንደሚበልጥ ነቢዩ (ሰዐወ) ስለነገሩን በሷ ተበራታ። ከፈጅር በኋላ እስከ ጸሐይ እስክትወጣ ምንም አይነት ሰላት መስገድ ክልክል ነው። ከዙሁር በፊት 4 ረከዓ ከዙሁር በኋላ 2 ረከዓ ከመጝሪብ በሗላ 2 ረከዓ ከዒሻ በሗላ 2 ረከዓ ከላይ የጠቀስኩልህን 12 ረከዓዎች የሰገደ አላህ በጀነት ቤት እንደሚገነባለት ነቢዩ (ሰዐወ) ነግረውናል። ከነዚህ ሱናዎች ውጭም የሚሰገድ ሰላት አለ። ከፈርድ ሰላት በፊትና በኋላ ከሚሰገዱ ሱናዎች ውጭ ያሉ የሱና ሰላቶችን አንተ ሁለት ሁለት፣ አራት አራት ... ረከዓ እያደረግክ ቀኑን ሙሉ መስገድ ትችላለህ። ሌላው በሌሊት የሚሰገደው ተሃጁድ/የለይል ሱና ሰላት ይባላል። በዚህ ስግደትህ ሁለት ሁለት፣ አራት አራት ረከዓ እያደረግክ የመጨረሻውን ዊትር 3 ረከዓ(ከፈለግክ 3ቱንም በአንዴ የመጀመሪያውንና ሁለተኛውን ቆመህ ሶስተኛውን ደግሞ ቁጭ ብለህ መጨረስ... ከዛ ውጭ ደግሞ 2 ረከዓ ሰግደህ የመጨረሻ ሶስተኛ ረከዓውን ለብቻው ትሰግዳለህ።) አድርገህ መስገድ ነው። ሁለት ሁለት፣ አራት አራት አድርገህ መስገድ ካልፈለግክ 3 ረከዓ ዊትርህን ብቻ መስገድ ትችላለህ። ላስታውስህ ምፈልገው ደግሞ የለይል/ የተሃጁድ ሰላት የሚሰገደው ዒሻ ከተሰገደ በኋላ እስከ ፈጅር ባለው ሰአት ነው። ከፈለግክ ሌሊቱን ሙሉ እየሰገድክ ማደር ትችላለህ። ነፍስህ ከምትችለው በላይ አታስገድዳት። የሱና ሰላት ጥቅሙ ፈርድ ሰላት ላይ ያጎደልከውን፣ ስህተትህን መሙላቱ ነው። የአንድ ስራ ተቀጣሪ ሆነህ ደመወዙ ባይበቃህ የጎን ስራዎችን ሰርተህ ገንዘብ አጊኝተህ ወጪህን መሸፈን እንደማለት ነው። በርታ አላህ ያጽናህ።
Jan 24, 2023