በአዲስ አበባ ከተማ የጥምቀት በዓልን ሳከብር ለ2ተኛ ጊዜዬ ነው፤ጥምቀት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በ30 አመቱ በማየ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ ተጠምቆ ልጅነቱን ያስመሰከረበት የኛን የእዳ(የኃጢአት) ደብዳቤ የደመሰሰበት ሃይማኖታዊ በዓል ነው፤በዓሉ ሃይማኖታዊና ትውፊታዊ ሥርዓቶች ያሉት ሲሆን በአብዛኞች ከተማ(በተለይ አአ) ከእምነቱ ተከታይ ማይጠበቅ፣ክርስቲያናዊ ያልሆነና እምነቱን የሚያሰድብ ተግባር ሲደረግ ማየት የተለመደ ሆኗል ይባስ ደሞ ሚገርመው ይሄን ለማድረግ የሚያቀርቡት ምክንያት ነው፤ለምሳሌ እከሌ ሲያደርግ አይቼ ነው፣አባቶች መች ከለከሉ(ይሄ እውነትም አያስጠይቃቸውም)፣ምን ችግር አለው፣ፈጣሪ እኛ ልጆቹ ደስ ሲለንኮ አይከፋውም...የመሳሰሉት የአላዋቂና የጅል ምክንያት ይደረድራሉ።በዓሉን ባከበርኩበት(አአ) በጣም ያዘንኩበት(በዋናነት ቤተክርስቲያን የምታዝንበት)ብዙ ነገሮችን አይቻለሁ -ቁማር -ዝሙት -ጭፈራ -ዘፈን -ድብድብ -መሰዳደብ ታድያ አንድ የሌላ እምነት ተከታይ ወገናችን ይሄን በዓል ተመልክቶ የኦርቶዶክሶች በዓልኮ እንዲ ነው ቢል ይፈረድበታል? #ጥያቄዬ...ምን እናድርግ ይሄን በተመለከተ?ነው!
Jan 19, 2023ይህ የማጠዉ ይመስለኘል ስሜታቸውን ስለምከተሉ ነው። ክርስትና የለመንፈስ ቅዱስ እንድ ነው ...... ማንም በክርስቶስ ቢሆን አድስ ፍጥረት ነው . ስለ ክርስቶስ ማመር የለባቸው ይመስለኛል እርሱ ይለውጣል
Jan 20, 2023