Guys echin tyake mokruat Under the proclamation 1265/2014 the government of Ethiopia establishes ‘The Ethiopian National Dialogue Commission’. What are the illustrated objectives of the commission?
Jan 19, 20232.1. የአገራዊ ምክክር ጥቅሞችና ዓላማዎች የአገራዊ ምክክር ጥቅም በዋናነት ግጭትን ለማስወገድ (peace building)፣ የፖለቲካና ዴሞክራሲ ሽግግርን ለማሳለጥ የሚጠቅም ነው፡፡ በተለይም ግጭቶችን ለመከላከል፣ ለማስተዳደር (conflict management) እና ለመፍታት አይነተኛ መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃም በበርካታ ሀገራት በተለየዩ ጊዜያት በተለያየ መነሻ ምክንያቶች ሀገራዊ ምክክሮችን አካሂደዋል፡፡ የተወሰኑት የተሳካለቸው ሲሆን በተወሰኑት የሚፈለገውን ግብ ሳያሳካ ቀርቷል፡፡ የሀገራዊ ምክክር አላማዎች መሰረታዊ የሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ያሉ ልዩነቶችን በማጥበብ መግባባትን ለመፍጠር፣ በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መካከልና ከመንግስት ጋር ያለን ግንኙነት ለማሻሻል፣ መተማመንን ለማጎልበት፣ የመነጋገር የፖለቲካ ባህልን ለማጎልበት፣ ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት፣ ጠንካራና ቅቡልነት ያለው አገረ መንግስት በጋራ ለመገንባት፣ ልዩነቶችን በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ለመፍታት፣ የዴሞክራሲና የፖለቲካ ሽግግር (transformation) ለማስቻል፣ ልማትን ለማፋጠን የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ በተጨማሪም የሀገራዊ ምክክር አላማ መሰረታዊ አለመግባባቶች፣ ልዩነቶችና ግጭቶች ምን እንደሆኑ መለየት፣ መሰረታዊ ምክንያታቸውን (root cause) መለየት እና በእነዚህ ላይ ልዩነቶችን በምክንያታዊ፣ በሰለጠነ፣ በመቻቻል መንገድ የጋራ መግባባቶች ላይ ለመድረስ እና የግጭቶቹ መንስኤ የሆኑ ልዩነቶችን ለማጥበብ ካልሆነም በልዩነቶች ላይ በመስማማት በሀሳብ ለመለያየት ብሎም ይህን የሀሳብ ልዩነት በዴሞክራሲያዊ፣ ሰላማዊና ህጋዊ መንገድ መፍታት የሚቻልበትን ዘዴ በጋራ በመቀየስ ተግባራዊ ለማድረግ ለመግባባት የጋራ ጥረት የሚደረግበት መድረክ ነው፡፡
Jan 20, 2023