ስለ ህግ ምታውቁ ሰዎች pls መልሱልኝ!!! አንድ ልጅ ከ35 አመት በፊት የሞተች እናቱን(አባቱ በህይወት አለ) ንብረት(መሬት) በፍርድ ቤት ጠይቆ ከአባቱ(የእናቱን ድርሻ) ማግኘት ይችላል?
Jan 19, 2023መጠየቅ ትችላለህ ነገር ግን አባትህ ይርጋን በመቃወሚያነት ካነሳ መውረስ አትችልም። ይህም ማለት አባትህ መሬቱን ከአስር አመት በላይ ስለያዝኩት ከሳሽ በይርጋ ይታገዳል ብሎ ሊቃወም ይችላል። ነገር ግን አንተም መሬቱን አብሬው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ እየተጠቀምክበት እንደሆነ በክስህ ላይ ጠቅሰህ ይህን ደሞ በምስክሮችህ ካስረዳህ የይርጋ መቃወሚያንም ማሸነፍ ትችላለህ #የህግ_ባለሙያ_አስተያየት_ነው
Jan 20, 2023