StarkOwl52471
#religion
ባህልን አክብሮ፣ ከእንስት ርቆ በዓመት አንድ ጊዜ፣ ጥምቀትን ጠብቆ ከኮረዳ መሀል፣ ከውብም ውብ መርጦ ልቡ እንደወደዳት፣ በውል አረጋግጦ ሎሚ በመወርወር፣ የሴት ደረት መትቶ ውቢቷ ኮረዳም፣ ደረቷ ሲመታ፣ ልቧ ተደስቶ ሚኖርበት ዘመን…. ሰው ከሰው ተጫጭቶ ሰው ከሰው ተጋብቶ ድሮ ቀረ ድሮ…. ሰው ከ”ውጭ” ተምሮ ባህል ተቀይሮ፣ ሎሚም ዋጋው ንሮ፣ አልሆነም ዘንድሮ….! ያሁኑ ጎረምሳ፣ ኮረዳ ለመቅረብ፣ ጥምቀት አይጠብቅም ያው ዓመቱን ሙሉ፣ ከሴት ጥግ አይርቅም። የኮረዳም ደረት፣ ለጥምቀቱ ሎሚ፣ አሻፈረኝ አለ ቀድሞ ተገላልጦ፣ አደባባይ ዋለ። መላኩ አላምረው ግጥሙ እንዴት ነው?
Jan 17, 20239 engagements