Hey 👋 Development bank of Ethiopia yamesataw siltana min min criteria mamaulat alabig ?
Jan 17, 2023ለሚመለከታችሁ ሁሉ ይህን እድል ተጠቀሙበት ። የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከወለድ ነፃ የብድር አገልግሎትን ጨምሮ በርካታ የብድር አይነቶችን አመቻችቼ እየጠበኳችሁ ነው ብሏል ። የብድሩ ተጠቃሚ መሆን የሚፈልግ ስልጠናውን የግደታ መውሰድ የሚኖርበት ሲሆን ስልጠናው ነፃ ነው ። ከዚያ በላይ ይህ ብድር ማስያዣ ወይንም Collateral የማይጠይቅ መሆኑ ተመራጭ ነውና መጠቀም የሚፈልግ ከስር ያለውንም መረጃ አብሮ ማንበብ ይችላል ። በአራተኛ ዙር የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች በሚሰጠው ስልጠና መሳተፍ ለምትፈልጉ በሙሉ፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ተደራሽነቱን በማስፋት የዲስትሪክቶቹን ቁጥር ከ12 ወደ 24፤ የቅርንጫፎቹን ቁጥር ደግሞ ወደ 108 በማሳደግ ይበልጥ በማሳደግ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በያዝነው የ2015 ግማሽ ዓመት ለአራተኛ ጊዜ የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ስልጠና ለመስጠት ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ ባንካችን እያደገ የመጣውን የሰልጣኞችን ፍላጎት እና ቁጥርን ታሳቢ በማድረግ ስራዎች ሲሰራ የቆየ ሲሆን፣ ለአራተኛውን ዙር ስልጠና ምዝገባም በ24 ከተሞች ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ የባንኩ ቅርንጫፎች ለማካሄድ ባንካችን ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ ተሳታፊዎች ሥልጠናውን ለመውሰድ የሚያስችላችሁን ምዝገባ ለማድረግ ከጥር 6 እስከ 16 ቀን 2015 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ ቅዳሜና እሁድ ጨምሮ በመላ የሀገሪቱ ከተሞች በሚገኙ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዲስትሪክቶች ስር በሚገኙ 108 ቅርንጫፎች ማለትም፡- 1. በአዲስ አበባ 2. ጎንደር 3. ባህርዳር 4. ደሴ 5. አሶሳ 6. ደብረብርሃን 7. ነቀምቴ 8. ሁመራ 9. ጅግጅጋ 10. አዳማ 11. ደብረማርቆስ 12. ወላይታ ሶዶ 13. ጅማ 14. ድሬዳዋ 15. ሻሸመኔ 16. ጎባ 17. መቐለ 18. ሽረ 19. ወልቂጤ 20. አርባምንጭ 21. ቦንጋ 22. ሐዋሳ 23. ሰመራ እና 24. ጋምቤላ 25. ሰቆጣ ከተሞች በሚቀርባችሁ አካባቢ በመሄድ እንድትመዘገቡ በአክብሮት እንጋብዛለን፡፡ በመሆኑም ተሳታፊዎች ከጥር 6 እስከ ጥር 16 ቀን 2015 ዓ.ም ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ባሉት ቀናት ተገኝታችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ በስልጠናው ለመሳተፍ ብቁ የሚያደርጉ የመመዝገቢያ መስፈርቶች፡- 1ኛ. ማንኛውም ሰልጣኝ ማንነቱን የሚገልጽ ማስረጃ ይዞ ወይም ህጋዊ ወኪሉ በአካል በአቅራቢያው በሚገኝ የባንኩ ቅርንጫፍ በመቅረብ መመዝገብ ይኖርበታል፣ 2ኛ. ሰልጣኞች የትምህርት ዝግጅታቸው ቢያንስ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ወይም በቀድሞው የ10ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ወይም በአሁኑ የ12ኛ ክፍልን ያጠናቀቁ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን ቀደም ብሎ በንግድ ስራ ላይ ቢያንስ ሶስት ዓመት ሲሰሩ የቆዩ ሆነው ህጋዊ የንግድ ፍቃድ በማቅረብ ስልጠናውን መሳተፍ የሚችል፣ 3ኛ. ሰልጣኙ በግል፣ በሽርክና ወይም በአክሲዮን ተደራጅቶ ለመስራት ፍላጎት፣ 4ኛ. ሰልጣኙ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ሳያቋርጥ መሰልጠን ይጠበቅበታል፣ በተጨማሪ ከአሁን ቀደም በእንስሳት ሃብት ልማት ዘርፍ ተመርቃችሁ በህብረት ስራ ኮሚሽን በኩል ምዝገባ ያካሄዳችሁ በሙሉ በአራተኛው ዙር ስልጠና መሳትፍ ስለሚጠበቅባቸው በአቅራቢያችሁ በሚገኙ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ቅርንጫፎች በመገኘት እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡ ባንካችን በቀጣይ የሚሰጣቸውን ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ለመጠቀም የተዘጋጃችሁ እና የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ሆናችሁ ስልጠና መውሰድ የምትፈልጉ በሙሉ በአቅራቢያችሁ በሚገኙ የባንካችን ቅርንጫፎች በመገኘትና በመመዝገብ ስልጠናውን መሳተፍ እንደምትችሉ እናሳውቃለን፡፡ ማሳሳቢያ ስልጠናውን ለአምስት ተከታታይ ቀናት ያልወሰደ ለሰርተፊኬት ብቁ አይሆንም፡፡ ባንኩ አዲስ ያቀረበውን የአክሲዎን አማራጭ በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎችን በባንካችን የማህበራዊ ትስስር ገጾች አልያም በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ቅርንጫፎች በአካል በመቅረብ የምታገኙ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የልማት አጋርዎ!
Jan 19, 2023