Tsome gehad nege ale ende esti yemiyawek kale nege new weys erob begemet sayhone
Jan 16, 2023⛪ ጥር 10⛪ ✟✝✞ ጾመ ገሃድ ✟✝✞ ገሃድ መገለጥ መታየት ነው፡፡ ❤ 👉 በጥምቀት መገለጥ መባሉ ሰው የሆነው አምላክ በዓለም ሲኖር እስከ 30 ዓመት እድሜው ድረስ ሰዎችን ለማዳን የመጣ መሲህ ሰው የሆነበት፣ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ እሱ መሆኑን ሳያውቁ ከኖሩ በኃላ በ 30 ዓመት እድሜው በባሕረ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ እጅ ሲጠመቅ አብ በደመና ሆኖ ‹‹የምወደው ልጄ ይህ ነው›› በማለቱ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል በራሱ ላይ ሲያርፍ በመታየቱ ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል ይሰቀላል ይሞታል ይነሳል ብለው የተናገሩለት መሲሕ እርሱ መሆኑ ተገልጦአልና፡ አንድም ሦስቱ አካላት በአንድ ጊዜ ታይተዋልና ምስጢረ ሥላሴ የተገለጠለት በመሆኑ ገሃድ ይባላል፡፡ (ማቴ 3፡13-17) ❤ 👉 ይህን በማሰብ የምንጾመው ጾም “የገሃድ ጾም” ይባላል፡፡ ቀኑም በዓለ ጥምቀት ከመዋሉ አንድ ቀን ቀድሞ ማለትም ጥር 10 ቀን ለ 11 አጥቢያ ነው፡፡ስለዚህ ጥር 10 ቀን ከ ሰባቱ አጽዋማት አንዱ የሆነው የገሃድ ጾም ነው ማለት ነው! ❤ 👉 ጥር 10 በዚች ዕለት ምንም ምን መብልን ሳይቀምሱ ምዕመናን ሁሉ እስከ ምሽት ይጾሙ ዘንድ ከኛ አስቀድመው የነበሩ ታላላቅ ሊቃውንት የቤተክርስቲያን መምህራን ሥርዐትን ሰሩ በምሽትም ቢሆን በታላቁ ጾም ከሚበላው በቀር ጥሉላትን እንዳይቀምሱ። ❤👉 በዚች ዕለት ምዕመናን እስከ ምሽት እንዲጾሙት ያዘዙበት ምክንያት ይህ ነው የልደቱና የጥምቀቱ በዓል በረቡዕ ወይም በአርብ ቀን ቢሆን በበዓለ ኃምሳ የሚበላውን የጥሉላን መብል በጥዋት በመብላት ምዕመናን ሁሉ በዓሉን እንዲያከብሩ የከበሩ አባቶች ሐዋርያት አዝዘዋል እሊህ ሁለት የእግዚአብሔር ታላላቅ በዓላቶች ናቸውና። መልካም በዓለ ጥምቀት ይሁንልን!!! From Hailu Mengesha
Jan 17, 2023