ኦርቶዶክሳውያን እርዱኝ እባካችሁ ለተወሰኑ ቀናት ጥቅሙንና ጉዳቱን እንዲሁም ሀጢአት መሆኑን ሳላውቅ masturbation😣😣 አደርግ ነበር ከማድረጌ በፊት ሀይማኖቴ ላይ ደህና ነበርኩ እና ስጋወደሙ እቀበል ነበር😥 ካደረኩ በኋላ ነገሮችን ሳነብ ና ስጠይቅ ከሀጢአትም የከፋ ሀጥያት መሆኑን አወኩ እና በቃ ደጁን ልረግጠው ራሱ ፈራለው ከፍ ብየ እንኳን ወደ መቅደስ ተጠግቼ አልሳለምም በጣም ነው እንደቆሸሽኩ ሚሰማኝ እና ከልቤ ተፀፅቼ ንሰሀም ገባሁ በራሴ በጣም ነው ያፈርኩት እና እንደበፊቱ ምስጢረ ቁርባንን መፈፀም: እንደገና የሱ ልጅ መሆን : በተክሊል ጋብቻ መፈፀም: የካህን ሚስት መሆን እችላለሁን? አመሠግናለሁ።
Jan 15, 2023“እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል።” — ሉቃስ 15፥7 ደስ ብሎኛል በጣም ስለ አንቺ እውነት ግን አንድ ነገር እወቂ እግዚአብሔር መሀሪ አምላክ ነው ዋናው የተሰበረ ልቦና እና መፀፀትን ነው የሚፈልገው ከኛ። ስለዚህ አሁን ጉባኤ ተካፈይ ፣ ባይብል አንብቢ እና በደንብ ፅኚ እምነትሽ ላይ አደራ! ለጥያቄሽ ትክክለኛ መልስ የምታገኚው ከአባቶች ስለሆነ የንስሀ አባትሽን አማክሪያቸው እስኪ
Jan 15, 2023