Ken keken sew mawrat eyastelagn new mayew sew hula yanaddegnal beteley minkelekel sew say betam yanaddegnal hulum eyasmesele new mimeslegn I lost my interests on everything I feel lonely ena labd yhon ede?
Jan 14, 2023የዚህ አይነት ችግር በተደጋጋሚ እዚህ መድረክ ላይ ጥያቄ ይጠይቃሉ ደበረኝ ሰለቸኝ ሞራል አጣሁ ሰነፍኩ ራሴን መቀየር አልቻልኩም እና ብዙ ይባላል ወዳጄ አንተ ብቻ አይደለህም በዚህ ጊዜ አብዛኛው ሰው ምንም እንኳን አውጥቶ አያዉራው እንጂ ዉስጡ ላይ እንደዚህ ነው። የችግሩ ምንጭ ምን ሊሆን ይችላል የሚለው ራሱን የቻለ አጀንዳ ነው ከሰው ሰውም የተለያየ ነገር ነው ነገር ግን አሁን ላይ ስለ መፍትሄው እናውራ። ነገር ግን ማሰብ ያለብህ ይሄንን ጥያቄ የጠየቅከር ይህ ችግር ስለመረረህ ስለሰለቸህ ማስተካከል ስለምትፈልግ ነው አይደል ስለዚህ ጥያቄ ጠይቀህ መፍትሄውን ሰምተህ ብቻ ዝም ሳይሆን እስከመጨረሻው ድረስ ለማስተካከል መታገል አለብህ። በጣም እርግጠኛ ሁኜ የምነግርህ ነገር ለዉጥ ሁሌም ይሰለቻል ለዉጥ ሰላም አይሰጥም እና በትክክል መለወጥ የሚችሉት ግን እየሰለቻቸውም ቢሆን ማድረግ ያለባቸውን ነገር ያደረጉ ራሳቸውን ያሰቃዩ ሰወች ናቸው። በ1ወቅት እኔም እንደዚህ ነበርኩ ምን አልባትም ከዚህም በላይ እናም ከ 4 እስከ 5 ወር ጊዜ ወስጄ ራሴ ላይ ሰራሁ የሚገርም ዘላቂ ለውጥ ራሴ ላይ ማምጣት ችያለሁ። እኔ የተከተልኩትን መንገድ አሁን እነግርሃለሁ 1. የመጀመሪያው ነገር በምታምነው እምነት ወደ መንፈሳዊ ህይወት ተጠጋ - ይህ ማለት ባንዴው መንፈሳዊ ሰው ሁን ሳይሆን ቢያንስ አዘውትረህ ወደ ቤተክርስቲያን ወይንም መስኪድ ሂድ ምንም እንኳን ባታደርግ ዝም ብለህ ደርስ ተመለስ ከቻልክ ደግሞ 1 ጥሩ ተለቅ ያለ ሰው ወይም ንስሃ አባት ያዝ እና ችግርህን አዋራቸው። እና ሌላው በቀን ዉስጥ ቢያንስ 15 ደቂቃ ጸሎት ማድረግ ልመድ እመነኝ ቀላል ነው ከ 24 ሰአት ዉስጥ ከ 15 - 30 ደቂቃ ለፈጣሪህ መስጠት በጣም ቀላል ነው ግን ልምድ ይጠይቃል እና ረጋ ብለህ ሳትሰለች በትንሽ ትንሹ መጸለይ ጀምር። 2.በቂ እረፍት አድርግ በደንብ ተኛ ቢያንስ በቀን ለ7 ሰአታት ያክል ተኛ። ማታ በጊዜ መተኛት ልመደ የማይጠቅሙህ ሰውች ጋር ከመጻጻፍ ወይንም ማይረባ ቪዲዮ ከማየት በጊዜ መተኛት እና ጠዋት ቀደም ብለህ መነሳት ልመድ 3.አመጋገብህን አስተካክል በቻልከው መጠን ሽሮም ሆነ ምስር በትክክል ለመመገብ ሞክር በአቅምህ balance የሆነ diet ለመመገብ ሞክር ሌላው ቢቀር ጎመን እና ቆስጣ በቀላል የሚገኝ ነገር እንኳን አንደፍርም አይደል ያን ካልቻልክ ደግሞ እንደምንም አንዴ ወጭ አውጥተህ multivitamin ግዛ እና ሁሌም በየቀኑ ከምግብ በኋላ ዉሰድ። 4.ስፖርት ስራ የግድ ጂም ወይም ብረት ቤት መሄድ የለብህም ቤትህ ዉስጥ ሆነህ በቻልከው መጠን ቢያንስ ለ30 ደቂቃ ተንቀሳቀስ ሌላው ቢቀር ጠዋት ተነስተህ ሩጥ ከቤትህ ፑሽአፕ ሴትአፕ ምናምን ስራ ብቻ ሁሌም ቀንህን በእንቅስቃሴ ጀምሮ ግዴታ አይደለም ግን ከቻልክ ሁሌም ወይም ሁሃ ባለበት ቀን ጠዋት ጠዋት ቀዝቃዛ ሻወር ዉሰድ እመነኝ ሞክረው በአካባቢህ የውሃ እጥረት ካለ ግን ችግር የለም መቅረት ሚችል ነገር ነው 5.መጽሃፍ አንብብ በጣም ወሳኙ ይህ ነው❗️ - የተለያዩ በጣም ጠቃሚ ምክር የያዙ መጽሃፍት አሉ እንሱን አንድ በ አንድ ቀስ እያልክ አንብባቸው ስታነብ ግን ልክ ለትምህርት እንደምታነበው በስነስርዓት ማስታወሻ እየያዝክ ምናምን መሆን አለበት። የግድ ማንበብ ያለብህ መጽሃፍት ብየ ማስባቸው 👉🏽 Atomic Habit (የልማድ አስደናቂ ሃይል) 👉🏽 The power of your subconscious mind (የውስጠ ህሊና ሃይል) 👉🏽 The power of Now (የአሁን ሃይል) 👉🏽 A new Earth ( አዲስ ምድር) 👉🏽 The purpose driven life (አላማ መር ህይወት) 👉🏽 The subtle art of not giving a fuck (የግድ የለሺነት ሚስጥር) 👉🏽 feel the fear and do it anyway (ፍርሃትህን አትፍራው ብትፈራውም ከማድረግ አታፈግፍግ) እና በመጨረሻም 👉🏽 ትልቅ ህልም አለኝ እመነኝ እነዚህን መጽሃፎች በትክክል ካነበብክ እና አድርግ የሚሉህን ካደረግክ ከምንም አይነት ቦታ ተነስትህ የምትፈልግበት ደረጃ ላይ ትደርሳለህ። የመግዛት አቅም ከሌለህ እኔ ሁሉንም መጽሃፎች እገዛልሃለሁ በኢንቦክስ አውራኝ ከላይ ያልኩህን አምስቱን ነገሮች ሳትሰለች እንደምንም እያስጠላህም ቢሆን በትክክል ከተገበርካቸው ሰላማዊ ደስተኛ ጤነኛ እና ስኬታማ ሰው የማትሆንበት ምንም ምክንያት የለም! 😃
Jan 15, 2023