ሰላም እንዴት ናችሁ ጥያቄው ለሰንበት ተማሪዎች ለሆናችሁ ወይም ለምታስተምሯቸው ሰዎች ነው የሰንበት ትምህርት አመሰራረቱ እንዴት ነው በጥንት ጊዜ አልነበረም በአብዛኛው የገጠር ክፍል የለም እና ማን ለምን ጀመረው እንዲሁም ከመዘመር ውጪ ምን ይደረጋል ? ሴቶች ከበሮ የሚመቱትና የሚወርቡ ለምንድን ነው ስርአት ነው ወይ???!
Jan 14, 2023የተጀመረው በግብጽ ሀገር በቅዱስ ማርቆስ የተመሠረተውን የእስክንድርያ መንፈሳዊ ት/ቤት አለቃ በነበረው በሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ ሀቢብ ጊዮርጊስ ነው። የመሠረተበት ዋነኛ ምክንያትም የምዕራባዊያን እምነት ተጽእኖዎችን ተቋቅመው ምእመናንን ከልጅነት እስከ ዕውቀት በሃይማኖታቸው እንዲጸኑ ነው። በኢትዮጵያ ደሞ ከዚ በፊት ያልነበረ ሲሆን በዛ ቦታ እብነት ት/ቤት እና በግል ደሞ ካህናት ህጻናትን ይሰበስቡ ነበር። ይህም ብቻ ሳይሆን በማኅበራትም ተደራጅተው ቤተክርስቲያንን የሚያገለግሉ ብዙ ነበሩ (እንደ ቅድስት ሥላሴና ምስካየ ህዙናን ከማኅበር ያደጉ ሰ/ት/ቤቶች ናቸው)። ግን የደርግ መንግሥት ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ መንግሥት ካስቀመጣቸው ማኅበራት ውጪ ሌሎች ላይ ጫና ማድረስ እና የተለያዩ ችግሮች የነበሩ በመሆናቸው ይሄን የወጣቶች ስብስብ የቤተክርስቲያን መዋቅር ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ በመሆኑ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ዘመነ ፓትርያርክ በ1970 ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ሰንበት ት/ቤቱ እንዲቋቋም ተደርጓል። አዎ። ሴቶች ከበሮ መምታት ብቻ ሳይሆን ቅኔ መዝረፍ፣ መወድስ፣ ዝማሬ መዋስእት ማድረግ ትችላለች። እንደነዚህ ያሉት ሴቶች ከተገኙ ግን በአብዛኛው በቤተደናግል ቢያደርጉ more ይመረጣል።
Jan 15, 2023