For Muslims Is There Any Evidence You Can Provide Islam Religion Is Before Mohammed. Ke Quran Wuchi?🤔
Jan 12, 2023በዚሁ ቻነል ላይ በቀን 12 ወርሃ May 2022 ከረፋዱ 4:00 ተጠይቆ የሰጠሁት መልስ ነው። "ቢረዝምም ታግሰህ አንብበው ኢስላም (إسلام) የሚለው የዐረብኛ ቃል ራስን (እጅ እግርህን.. ሁለመናህን) ለፈጣሪ ማስገዛት ወይም መስጠት ማለት ሲሆን ሙስሊም (مسلم) ማለት ደግሞ ራሱን ለፈጣሪው ያስገዛ አማኝ ግለሰብ ነው። *አላህ የሚለው ቃል 'ኢላህ' ከሚለው ቃል የመጣ ሲሆን 'ጌታ' የሚል ትርጉም ይሰጠናል። (ስህተት ሊኖር ስለሚችል ከኔ የተሻለ እውቀት ያለው ቢያርመኝ የተሻለ ነው። ለበለጠ መረጃ የወሒድ ዑመርን ቻናሎች መከታተል ይቻላል https://t.me/Wahidcom) ይህን መሰረት በማድረግ አላህ ይህችን ምድር ፈጥሮ ከኛ በፊት የኖሩት ኖረው አብቅተው በክፋታቸው አጥፍቶና ቀሪዎቹን ከበታተናቸው ኋላ እኛን ፈጥሮ እንድንኖርባት አደረገን። አላህ አደምና ዝርዮቹ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ነቢያትን ቀስቅሷል። ሁሉም ነቢያት በፈጣሪያቸው ትዕዛዝ ስር የነበሩ ራሳቸውን ለፈጣሪያቸው ያስገዙ አማኒያን ነበሩ። በፈጣሪ/አላህ እገዛም ሁሉም ነቢያት ህዝቦቻቸውን ለማሳመን የተለያዩ ተዓምራትን ተጠቅመዋል። ለምሳሌ:- ሷሊሕ - ግመል ተራራ ሰንጥቃ እንድትወጣ አድርጓል ሙሳ - እንጨትን ወደ እባብ፣ ባህርን ሰንጥቆ ህዝቦቹን ማሳለፍ ከመዳፉ ብርሃን መታየት.... ሱለይማን - ነፋስ እና አጋንንት ገርተውለት በነሱ ወደፈለገበት አይንን ጨፍኖ በመክፈት ፍጥነት መንቀሳቀስ ዒሳ - ያለ አባት ከእናት ብቻ መወለድ፣ በእጁ እርግብ ሰርቶ ኡፍ ሲላት ህይወት ዘርታ መብረር... ሙሐመድ - የሱን እዚህ መግለፅ ራስን ማድከም ነው! ከ 3000 በላይ ተዓምራት አሉት። ጨረቃ ለሁለት መሰንጠቋ፣ የተዓምራቶች ሁሉ ተዓምር የተከበረው ቁርዓን፣ እና ሌሎች ነቢያቶችም ሌሎች ተዓምራቶች ነበሯቸው። ከርዕሱ ባይገናኝም ልብ ማለት ያለብህ ሁሉም ነቢያት ይህን ሁሉ ተዓምር የሰሩት በራሳቸው አቅምና ችሎታ ሳይሆን #በፈጣሪያቸው_ፈቃድና_ችሎታ_ነው! ተዓምራቶችንም ሲያሳዩ የነበሩት ፈጣሪያቸውን በመካድ ጣዖታትን ሲገዙ የነበሩ ህዝቦችን ወደ ፈጣሪያቸው ለመመለስ ነው። ሌላ ዐላማ የለውም። ብዙዎች መስመር የመሳቱት በዚህ ነው። አላህም ነግሮናል። የሁዶች ዑዘይር የአላህ ልጅ ነው አሉ። ነሳራዎች/ክርስቲያኖች መሲሕ ዒሳ የአላህ ልጅ ነው አሉ። ይህ የሆነው ህዝቦቻቸው ያሳዩትን ተዓምራት አግንነው እና በራሳቸው በፈቃድህ እንዳደረጉ በማሰባቸው ነው። አንዳቸውም በራሳቸው ፈቃድ ያደረጉት ነገር የለም! ሲጀመርም ይህችን ምድር የረገጡት በፈጣሪያቸው ፈቃድ ነው። ወደ ጥያቄህ ልመለስ ... ከዚያም ተዓምራቶችን በማየትና በማስተንተን "ይህ ከፈጣሪ ቢሆን እንጂ ከማንም አይደለም" ብለው በጊዜያቸው የነበሩ ነቢያትን አምነው ከፈጣሪ ትዕዛዝ የተላከላቸውን ተግብረው የኖሩ አሉ፣ አሻፈረን ብለው በዛው ጥመታቸው የሄዱ አሉ። ያመኑት አካላት ራሳቸውን ለፈጣሪያቸው ሁሉ ነገራቸውን በመስጠታቸው በዐረብኛው ሙስሊም (ነጠላ) ወይም ሙስሊሙን (ብዙ ቁጥር) ይባላሉ። ትክክል ነኝ ብሎ አምኖ እንኳ ከአላህ ውጭ ሌላን ያመለከ ሰው አማኝ ልንለው አንችልም። በአጭሩ ያላመነ፣ ከሀዲ/ካፊር ነው የሚባለው። ስጨርስልህ አላህ ፈጥሮት በአላህ ያመነ ፍጡር ሁሉ ከአደም አንስቶ እስከ መጨረሻው ድረስ ያለ ሙስሊም ይባላል። ብዙዎች ሙስሊም ሲባል የሚያስቡት ቀጥታ ከሙሐመድ በኋላ ያለውን የሙሐመድ ተከታይ ብቻ ነው። ነገር ግን ሁሉም በራሱ ቋንቋ ሙስሊም የምትለዋን ቃል በራሱ ተጠቅሞ ስላለፈ ኢስላም አዲስ እምነት አይደለም። ለምሳሌ እኔ በአላህ አምኜ ያዘዘኝን እስከሰራሁ ድረስ በቋንቋዬ #አማኝ ነኝ። በጀነቱ ቋንቋችን ደግሞ #ሙስሊም ነኝ። አማኝ=ሙስሊም ሙስሊም ያልሆናችሁ ይህን ማንበብ ትችላላችሁ። ለመሳደብና አሉታዊ ነገርን ልትሞነጭሩብኝ አትምጡ። ሙስሊም የሆነ ስህተቴን ቢያርመኝ ደስ ይለኛል። እቀበላለሁ።" የቃላት ግድፈቶቼን እንኳ አላስተካከልኩም። ወደ ኋላ ተመልሰህ ማንበብ ትችላለህ። ጥያቄህ እንደተመለሰ ተስፋ አደርጋለሁ። ካልተመለሰልህ አሳውቀኝ። አንተም ከመፅሐፍ ቅዱስ ውጭ ከኢየሱስ በፊት (እንደውም ኢየሱስን ጨምሮ) ስለክርስትና የሚያውቅ ነቢይ፣ ቅዱሳን ወይም ህዝብ ልትነግረኝ ትችላለህ?
Jan 12, 2023