ለመጽሐፍ ቅዱስ አንባቢያን ምን መሰላችሁ... "ሴቲቱም፡ዛፉ፡ለመብላት፡ያማረ፡እንደ፡ኾነ፥ለዐይንም፡እንደሚያስጐመዥ፥ለጥበብም፡መልካም፡ እንደ፡ኾነ፡አየች፤ከፍሬውም፡ወሰደችና፡በላች፤ለባሏም፡ደግሞ፡ሰጠችው፡ርሱም፡ከርሷ፡ጋራ፡በላ።" ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ 3÷6 ከዛ ቀጥሎ ቁጥር 7 ላይ "የኹለቱም፡ዐይኖች፡ተከፈቱ፥እነርሱም፡ዕራቍታቸውን፡እንደ፡ኾኑ፡ዐወቁ፤የበለስንም፡ቅጠሎች ፡ሰፍተው፡ለእነርሱ፡ለራሳቸው፡ግልድም፡አደረጉ።" ይላል። ወደ ጥያቄዬ ስመለስ የላይኛው ላይ "ለጥበብም መልካም እንደሆነ አየች" ይላል። ሁለተኛው ላይ ደግሞ "የሁለቱም አይኖች ተከፈቱ" የላል እና እንዴት የመጀሪው ላይ "አየች" የሚ ለው ከታችኛው ጋር አይጣረስም?? ማለት አይናቸው ሳይገለጥ.... በቀናነት መልሱልኝ። ምንም እውቀቱ ስለሌለኝ ነው።
Jan 11, 2023የመጀመሪያው የሚያዩበት የስጋ አይን ነው። ሁለተኛው ግን የውስጥ አይን ነው፣ ማስተዋል ምናልባት ልንለው እንችላለን። መጀመሪያ ራቁት ሆነውም ምንም አይመስላቸውም ምክንያቱም የውስጥ አይናቸው ስለማያይ እና ስለማያስተውሉ፤ ፍሬውን ከበሉ በኋላ የውስጥ አይናቸው ተገለጠና ራቁት መሆናቸው አሳፍሯቸው መተፋፈር ጀመሩ። ህፃን ልጅ ለምሳሌ ልጅ እራቁት መሆኑ ምንም አይመስለውም ኖርማል ነው፣ ሲያድግ እና ሲያስተውል ግን ያፍራል፣ ይሸፍናል። ከተሳሳትኩ አርሙኝ ወይም ጨምራችሁ አስረዱት።
Jan 11, 2023