Before I lost my life Someone help me out here ሀገር ዉስጥ አይደለም የምኖረው እና - ማታ ማታ እንቅልፍ በሰዓት አለመተኛት - ሙሉ ቀን የድካም ስሜት መሰማት - የምግብ ፍላጎት መቀነስ እና የተዛባ ለሰዉነት የማይጠቅሙ ምግቦችን ለስላሳ እና ሌሎች ጣፋጭ ነገሮችን ማዘዉተር - ለነገሮች ስልቹ መሆን ትግስት ማጣት - ከቤት መዉጣት እና ሰው ጋር መገናኘት አለመፈለግ - ከጉአደኛም ጋር ሆነ ቤተሰብ ጋር የማዉራት ፍላጎት መቀነስ - ደስተኛ የሚያደርግ ፊልም ዘፈን ወይም ምንም አይነት የሚያዝናና ነገር አለማግኘት - አልፎ አልፎ ፖርን ማየት እና በየቀኑ ማስተርቤት ማድረግ - ፆምም ሆነ ፀሎት ባጠቃላይ መንፈሳዊ ነገር ላይ በጣም መሰላቸት - ለምን ነው የምኖረው ብሎ ግራ መጋባት እና ስለወደፊቱ ከሚገባው በላይ እያሰቡ መጨናነቅ - ሙሉ ቀን ላፕቶፕ ወይም ስልክ ይዞ አልጋ ዉስጥ ቁጭ ብሎ መዋል ብቻ መፈለግ - ራስን መንከባከብ መጥላት I know it's not normal, what shall i do to become a normal Person
Jan 08, 2023እኔም(ሀገር ውስጥ ብሆንም) ከዚ ጋር ተቀራራቢ የሆነ ነገር በተወሰነ መልኩ ይገጥመኛል ፤ ታዲያ ትልቅ መፍትሄ የሆነልኝ ሁሌ ጠዋት ጠዋት ቀዝቀዝ ያለ ወይም ለብ ያለ ሻወር እየወሰድኩ (እንዲሁም በቀኑ እና በማታውም ቢሆን ዱካኩ እና ድካሙ ሲበዛብኝ እየወሰድኩ) እንዲሁም ብዙ ቀን በተለይ ፀሀይ መውጫና መግቢያ ሰአት walk እያደረኩኝ እና እየተዝናናሁ በማሳለፍ ጭንቀቷን ፣ ትእግስትት ማጣትን ፣ የምግብ ፍላጎት ማጣትን ፤የሁል ቀን ድካምን እና የእንቅልፍ ማጣትን መቀነስ ችያለሁ። የትም ቦታ ማለትም ከተማ ውሶጥ፣ መናፈሻ ፣ ገጠራማ ቦታ እና ሌላም ቦታ አመቺ ለዚ አመቺ ነው ውጪ ሀገር ደሞ የበለጠ ሚመች መሰለኝ። በሱ ላይ ደግሞ ትንሽና ቀለል ያሉ ስፖርቶችን ስሰራ ልዩ የሆነ ለውጥ ነው ያየሁት። እንዲሁም ይሄ walk ማረጉና በተፈጥሮ መመሰጡ ትንሽ ወደ ሀይማኖተኝነቱ የመለሰኝ ይመስለኛል፤ ሀይማኖተኝነቱ ደሞ የ ፖና ማስ*ን ነገር ይቀንሰዋል። በተጨማሪም ትንሽ የሚያዝናኑ ወጎችን የያዙ መፅሀፎችን እና ጦማሮችን/blogs ማንበብ እና እንደዚህ አይነት ቀለል ያሉና "ወገኛ" ፊልሞችን ማየትም ስራ ላለመፍታት አግዘውኛል ፤ እንዲሁም በነሱ ስፍታታ ከሰውም ጋር ለመግባባት ትልቅ መፍቶሄ ሆኖልኛል። ራሴንም ለመንከባከብ መነሳሳቶን እነዚ ነገሮች ፈጥረውልኛል plus የተለያዩ የንፅሀሰና /ውበት እቃዎችን ማሟላትም ለዚህ ይረዳል። ከስልክ/ ላፕቶፕ ጋር ያለው ቁርኝት ደሞ በነዚህ ነገሮች መሟላት ሚሻሻል ሲሆን screen time management አፕሊኬሽኖችን ማስጫን ደሞ በጣም ያግዛል። በነዚህ ነገሮች ላይ ደሞ አዲስ ሞያ መልመድ/ የነበረን መልሶ መስራት ወይም ማዳበር ከተጨመረ ቶልቅ ለዌጥ ማምጣት ትችላለህ/ትችያለሽ ማለት ነው። ብቻ ቁርጠኝነት እና ቋሚነት /ዘላቂነት ትልቅ ጎዴታ ነው ።
Jan 08, 2023