ሠላም ቤተሰብ ምን ይሻላል አደንቁረው ሊጨረሱኝ ነው ውይይይ ቤተሰብ .....አረ ልጄ አግቢ ህብረተሰብ ... ይቺ ልጅ አታገባም እንዴ ቆማ ቀረች እኮ ጓደኞቼ .....ባል እናጣብስሽ እናምጣልሽ አግቢ others .....ምነው እስካሁን ? ወንድ ጠፍቶ ነው? ብላ ብላ ብላ እኔ... 25 አመቴ ወንድ መጣ ቀረ አይሞቀኝ አይበርደኝ ይሄን ጥያቄ የማልሰማው ግን የትአባቴ ብገባ ነው ?? 😂
Jan 06, 2023ዙርያሽ ያሉ ሰዎች ለሚሉት ነገር ቦታ አትስጪ። እንደዚህ እንዲሉሽ ያረጋቸው ነገር በነሱ አረዳድ ስኬት ማለት ተጠልፈውም ይሁን ተሸኝተው ጥሩ ኑሮ አለው የሚባልለትን ሰው (ገረድም ሆነው ) አግብተው መውለድ ነው። በርግጥ እኔ በእድሜዬ ገና ትንሽ እና ለጋብቻ የማልበቃ ብሆንም፤ ነገ ባገባ የማገባት ሴት ብዬ ካስቀመጥኩት መስፈርት አንዱ እድሜዋ ከ26 በላይ የሚል ነው። እንደ ምክንያት የማቀርበው ደሞ ከዚ እድሜ በታች ያሉት ሴቶች ተማሪ፣ ወይ ገና አዲስ ተመርቀው ሥራ ሳይዙ በቤተሰብ ተጠግተው ከራሳቸው ጋር የሚጣሉ ናቸው። እንደነዚህ ያለችን ሴት የራሷ የሆነ financial stability ስለሌላት የራሷን ህልውና ከኔ ኪስ እና ካዝና ጋር ታያይዛለች። ይሄ ደሞ ለኔ ሚስትነት ሳይሆን ገረድነት ወይም ልጅ መፈልፈያነት ነው። ለኔ ስኬታማ ሴት ማለት ተምራ ባላት እውቀቷ የምትተማመን፣ ሰርታም በስራዋ በምታስገባው ገቢ (ትንሽም ይሁን ትልቅ) እራሷን ማስተዳደር እንደምትችል የምታምን፣ ወንድን በተለምዶ "ብቁ ነው" የሚያስብሉ ነገሮችን ይዛ ስትገኝ ነው። እንደዚህ ያሉ ሴቶች ቢያገቡ በራስ መተማመናቸው እና ቤተሰብ አስተዳደር ብቃታቸው perfect የሚባል ዓይነት ስለሆነ ይሄንን ስኬት ደሞ በለጋ እድሜሽ በቀላሉ ሊገኝ የሚችል አይደለም። እናም የኔ እህት፤ የምነግርሽ ነገር፦ ሥሪ፣ ታታሪ ብርቱ ስኬታማ ሴት ሁኚ። ደሞ 25 ዓመት ረፍዷል አይባልም። Even my older sister (24) doesn't seem she is going to marry in these 2 year. አሁን ባላት ሥራ ሰርታ ነገ ማግባቷ ባይቀርም፥ believe me ማንም በህልሙ እንኳም የማያገኛት ዓይነት high class ሴት ሆና ነው የምታገባው። ሳጠቃልል፥ ለሰው ወሬ ቦታ አትስጪ። ማንም ሰው የሚያወራው እስከሚያውቀው ያህል ነው።
Jan 07, 2023