Betam mafikerew ena mesasalet saw ale tenesh were aberen honenal gen enen sayi hone lela set new esu miyafekerew ejige betam tamemiku bey sametu hospital gebich samet tegnch mnmn new mewetaw ahun chirash ye ebed medanite eyewakiw new ene esun metaw alechilem emotalew lesum bezu geze negerewalew gen beka lebe teseber memot lene erefet new teyiw malet lene mote new ebakachu ke lebe yimenech meker setugn ebede ayedelewm fiker becha new yeyazegn
Jan 06, 2023ፍቅር አደለም የያዘሽ... ልጁ ሱስ ሆኖብሻል ፣ ከዛ ደሞ የሆነ የሚገርም የመርሳት መንፈስም የያዘሽ ይመስለኛል ሳታውቂው የኖርሽበት አመታትን ረስተሻቸዋል... ደስታ ብቻ መፈለግ ብቻ ማግኘት ብቻ ነው ኑሮ ህይወት ብለሽ ማሰብ ጀምረሻል ባታውቂውም ራስሽን እየገደልሽ ነው... ማፍቀርን እንደ አሪፍ ነገር አስተምረውሽ ይሆናል ስታድጊ ግን ሱስ በየቱ መልክ ነው ልክ ሊሆን የሚችለው?!... ባርነት እንዴት ፍቅርን ሊተካ ይችላል?... ምናልባት ባንቺ ቦታ ስላልቆምኩ ይሆናል እንደዚህ የወቀስኩሽ ግን ለምን እኔ ባንቺ ቦታ አልቆምኩም... ሱስ noble ነገር ቢሆን ኖሮ እ? መተው መቻልን የመሰለ ነገር የለም... ልተወው ብል እንኳን አልችልም የምትይው ነገር ሁሉ በፍቃድሽ የገባሽበት ባርነት ነው የሚሆነው... ደሞ ሞትን እንደመጨረሻ ማየት የት ያደርስናነው ካለሱ እሞታለሁ የምትይው?... ያንቺ ሞት ምን የሚያመጣው ለውጥ አለ? በባርነት ሞተች ከመባል የዘለለ ታሪክ አይኖርሽም እኮ... እስቲ ታሪክሽን አሳምሪው አትሊስት... ከ መሞትሽ በፊት ኑሪ መጀመሪያ ይሄ ኑርሮ አደለም... መኖር ሁሉንም ነው ማግኘቱንም ማጣቱንም መያዝንም መተው መልቀቅንም... መደሰትም ማዘንንም ነው መርጬ እኔ የፈለኩትን ብሎ መገገም ቀስ በቀስ መሞት ነው... እና እንደኖረ ሰው እሞታለሁ አትበይ... እየኖርሽ አደለም ፣ ይሄ ካጣሁት እቆረጣለሁ እፈለጣለሁ የሚለውን ተይው ራስሽን አጥተሽ ሌላ ሰው ማግኘት የለምና... በርግጠኝነት ምነግርሽ እኔ ልጁን ብሆን አጠገብሽም አልደርስም ምክንያቱም ራሱን የከዳ ሰው ለፍቅር ይታመናል ብዬ አላስብማ... ሳይሽ ፍላጎት ምኞት አምጣ አምጣ የሚል መንፈስ ነው የሚታየኝ ከዛ ውጪ... ህይወት ይኑርሽ ፣ እኔ የምትይው የምትታመኚለት ፀባይ ባሕርይ character ይኑርሽ ፣ ለራስሽ ክብር ይኑርሽ... ራስን መጣል አያኮራም ፣ ህልም መንገድ ይኑርሽ አላማ( such a cliché word) ይኑርሽ ያልኖረን ሰው ማን ይፈልገዋል?... አንቺ ራሱ አይደብርሽም እንዴ? የሆነ የምትኮሪበት ሰው ሳትሆኚ የሆነ እኔ የምትይው standard ሳይኖርሽ ካልተወደድኩ ብሎ መጠበቅ አለ እንዴ? ምንም ከሌለሽ ማንም አይፈልግሽም ስለዚህ ይኑርሽ... መጀመሪያ ማንነትሽን ስሪ እኔ የምትዪው ሃሳብ ይኑርሽ... ሌላ ወጪ አይጠይቅም
Jan 07, 2023