Ere guy’s yhe neger betam awezagebegn esti mndnw???? ያዕቆብም እግዚኣብሄርን ፊት ለፊት አየው ”(ኦሪት ዘፍጥረት 32:30) “እግዚኣብሄርን ያየው አንድ ስንኳ የለም” (የዮሐንስ ወንጌል 1:18)----------- Clash ayaregm???
Jan 05, 2023“መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው።” — ዮሐንስ 1፥18 ያዕቆብም ሙሴም ኢሳይያስም ያዩት እግዚአብሔር ወልድን ነው ዮሐንስ እየተናገረ ያለው ስለ እግዚአብሔር አብ ነው። ይህን ምናውቀው ጳውሎስ ደግሞ ወልድ የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው ይለዋል ፤ “እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው፤ የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው፤ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል፤” — ቆላስይስ 1፥15-16 ሥሉስ በሆነ አሃዱ አምላክ እናምናለን።
Jan 05, 2023