selam sewoch andi tyake neberegn hulet akistoch alugn ena betam esistoch nachw yeteleyaye hager new minorut ena egna ga mimetuti leselam aydelem I'm sure tinkola endastonekolubin to me ,my mom, my older brother and little sister ena erase laym aychalew destaye ayzelkim beka hulle endeteseberkugn new ke andem hulete bene akim tilk milachewn genzeb atichalew be seraye ena mn yshalegnal ahun yegna beteseb ye chigr meceresha lay nen inatachn andi negr bitihon yegna bet mebetenu new ena ye tanash ehte eda ene lay new miwedkew talak wendme serto metet new ena mn yshalegnal btm cenqogn ebet mader erasu akumealew . hasabachun bitagarugn ameseginalew
Jan 04, 2023ያልሆነ ነገር ወስደህ የማይሆን ሃሳብ ውስጥ አትግባ። ጥንቆላም መተትም whatever የሚደርስብህ ካመንክበት ብቻ እንጂ አንተ ጋ የሚደርስበት አንድም ምክንያት የለም። ያንተ ደስታ የማይዘልቀው አንድም የዓለም ደስታ ዘላቂ ባለመሆኑ፣ እንዲሁም ደሞ ያንተ ደስታ በእግዚአብሔር ስላልሆነ ነው። ደስተኛ መሆን ከፈልግክ ለተሰጠህ ትንሽ ነገር አመስግን፣ በደስታህ ጊዜ እግዚአብሔር ዐስብ፣ በሐዘንህ ጊዜ ዐስበው እንጂ በስሙ አታማርር። በማማረር ከኖርክ መቼም ዘላቂ ደስታ አታገኝም። በቤተሰብ ከሆነ እኛም በተመሳሳይ ሳይሆን ከዚ የከፋ ነገር አጋጥሞናል። ወላጅ አባቴ ማንም ለጠላቱ የማይመኘውን ህመም ታሞአል፣ እናቴም እሱን ለማሳከም ስትል ያለሁለታቸው ለ3 ዓመታት ከታንሽ ወንድሜና ታላቅ እህቴ ጋር ኖሬያለው፣ ሴት አያቴ የአባቴን መታመም ሰምታ በዛው ታማለች፣ እኛም ለጊዜው financially ተጎድተን ነበር (የቤት ደሞዝ አልበቃ ብሎ በህዝብ እርዳታ ነበር ህይወቱ ሲያስቀጥል የነበረው)።..... ባጠቃላይ ከውጭ እያየን የነበረ ሰው ይሄንን ሲያዩ "ጥንቆላ ይሁን ተንኮል ይሁን እገሌ ትሁን እገሌ ይሁን" እያሉ ስንት ነገር ሲናገሩ እኛ በቤት ያለነው ያለን መግባባት እና መተሳሰብን ደሞ ሲያዩ እንቆቅልሽ ይሆንባቸዋል። ከውጭ ለሚያዩት እንጂ ውስጥ የነበርነው ምንም ነገር መስሎ አልታየንም። ለያንዳንዱ ነገር በእግዚአብሔር ደስ መሰኘታችን በሆነው ባልሆነው እንዳናማርር አርጎናል። እና አሁን አባቴ በህይወት የለም። በህማሙ ጊዜ፥ አይደለም ሰውና አምላክን፤ አልጋውን ራሱ አመሰገናት እንጂ አላማረረም። ባጠቃላይ ከትልቁ ፈተና እረፉ ሲለን የሱን ነፍስ ለንሰሐ አብቅቶ አሳረፈው። ትቶ የሄደውን ቤቱን ደሞ ጸጋ በጸጋ አደረገው። እኛ ልጆቹም ለመልካም ቦታ በቃን፥ የዛኔ ብዙ ነገሮችን suffer ያረገችው ታላቅ እህቴ ከሚሊዮን አንድ ሰው የሚያገኘውን ትልቅ የሚባለውን ዕንቁ እድል አገኘች። እና ልልህ የፈለግኩት ለሚያጋጥምህ ነገሮች በሰው ጣትህን አትቀስር፥ ፈጣሪንም አታማርር። ምንም ቢመጣ እሱ ሰጠ እሱ ነሳ ብለህ በጸጋ ተቀበል።
Jan 05, 2023