የኔ ጥያቄ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በየወሩ ማህበር በማዘጋጀት የተለያዩ አማልክትን ይዘክራሉ ለምሳሌ ፣ገብርኤል፣ሚካኤል፣ማርያም.... እኔ መጠየቅ የፈለኩት የማህበሩ አባላት ወሩ ደርሶአቸው ለፍተው ጥረው ግረው ይደግሱና ድግሱ ግን የሚሆነው ለማህበሩ አባላት እና ግፋ ቢል ለአካባቢው ሰዎች ነው የኔ ጥያቄ የተዘጋጀውን ማእድ ለምን ለቸገራቸው የቀን ጉርስ ላጡ ሰዎች ማድረግ አልተቻለም??
Jan 03, 2023ወንድሜ በመጀመርያ አማልክት አደሉም የምናመልከው አንድ አምላክ እግዚአብሔርን ነው መላዕክት እና ፃድቃን ሰማዕታትን እዘክራለን ድግሱም ያን ያህል ሰፋ ያለ ዝግጅት ስለማይደረግበት እና ቀኑን ለማሰብ ነው እንጂ በዋናነት ለነዳያን ነው እኮ 🙏🙏🙏
Jan 04, 2023