Protestants ...tselot stadergu MN MN eyalachhu nw mittselyu ??? bedenb litsflgn michl sew pls Thanku 😍
Jan 01, 2023እግዚአብሔር አባት ሆይ በፊትህ እንድሆን ዕድልን ስለሰጠኸኝ በኢየሱስ ስም አመሰግናለሁ። ምህረትህን በህይወቴ ስላበዛህ፣ ከነሀጢያቴ ወደኸኝ በልጅህ ሞት በኩል ከራስህ ጋር ስላስታረከኝ፣ ስላዳንከኝ፣ በክርስቶስ ስራ በማመን የሚገኘውን ፅድቅ ስለሰጠኸኝ፣ የዘላለም ህይወትን በክርስቶስ ስለሰጠኸኝ አመሰግናለሁ። በድካሜ የሚያበረታኝን ጸጋ ስለሰጠኸኝ፣ ስለወደድከኝ አመሰግናለሁ። ጌታ ሆይ ዘመኔን በሙሉ፣ ቀኖቼን በሙሉ እንደቃልህና እንደሀሳብህ እንድኖር ጸጋህ ይርዳኝ። አባት ሆይ በህይወቴ አንተ ፈቅደህ ስለሚሆነው ነገር ሁሉ እባርክሃለሁ። አባት ሆይ ደግሞ ይሄ ና ያ ጉዳይ እንዳስጨነቀኝ ታውቃለህ፣ በኢየሱስ ስም እርዳኝ። 'እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉ' ተብሎ በቃል እንደተጻፈ ዛሬም እነዚህን ያስጨነቁኝን ጉዳዮች በፊትህ አስቀምጣለሁ፣ አንተ ስለምትመልሳቸው እና ከጭንቀቴ ስለምታሳርፈኝ ተመስገን። በሁሉ ግን አንተ የምትመርጥልኝ የተሻለውን ነውና እንደኔ ሀሳብ ሳይሆን እንደፈቃድህ ይሁንልኝ። ዕለት ዕለት በፊትህ እንድሆንና ቃልህን እንዳጠና ጸጋህ ያበርታኝ። ወደ እውነት ሁሉ የሚመራው መንፈስ ቅዱስ የቃልህን ፍቺ ያብራልኝ፣ መረዳቱን ይጨምርልኝ። አባት ሆይ ጓደኞቼ እና x y z ደግሞ አንተን ወደ ማወቅ እንዲመጡ እና ቃልህ እንደሚል የመዳን ብቸኛው መንገድ በክርስቶስ ኢየሱስ የመስቀል ስራ በማመን መሆኑን አውቀው እንዲያምኑና፣ የህይወትን መንገድ መንፈስ ቅዱስ በልባቸው እንድታበራ በኢየሱስ ስም ጸለይኩ። አባት ሆይ ያልዳኑ የጠፉ በጎችህ ሁሉ አምነው እንዲድኑ በኢየሱስ ስም እጸልያለሁ። እኔ ልጅህም ይህንን የመዳን እውነት እና ህይወት መመስከር እንድችል መንፈስህ ያበርታኝ። ዛሬ በምሰራው ስራ ፍሬያማ እንድሆን እርዳኝ። ስለ ሁሉ ተባረክ። በኢየሱስ ስም ጸለይኩ፤ አሜን። #ይሄ ለምሳሌ ነው። ፀሎት ፎርሙላ የለውም። መንፈስ ቅዱስ ልባችንን ባሳሰበው ርዕስ ላይ ሁሉ እንጸልያለን።
Jan 02, 2023