የተለያየ ሀይማኖት ነህ እና ልጅቷ ከምነግራችሁ በላይ ተፈላጊ ናት የማይጠይቃት ሰው የለም።እና በአካል ማንም ሳያውቅ በጣም እንገናኛለን እና መሳሳም ትፈልጋለች እኔ ደግሞ ባንሳሳም እፈልጋለሁ።so what shall i do?
Dec 31, 2022ሰላም የተወደድክ ወንድሜ እንዴት ነህ? እኔ ባለሁበት ቦታ ደህና ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን! ለጠየቅከው ጥያቄ የሚሆን መልስ እነሆ! ያለህበት ሐይማኖት እንዳለ ሆኖ ባለህበት ሐይማኖት ከጋብቻ በፊት መሳሳም ይፈቀዳል? እኔ አላውቅም ብትለኝ እኔ ባለሁበት ሐይማኖት ፣ በማምነውም አምነት አይፈቀድም። ሌላው ደግሞ በምንም ሐይማኖት ውስጥ ሁን መሳሳም ወደዝሙት የሚያደርስ መንገድ ነው። ሌላ ጥያቄ ልጠይቅህ ዘላለማዊ ደስታ በማይገኝበት የዝሙት አለም ውስጥ ተጨማልቀህ መኖር ትፈልጋለህ? የማትፈልግ ከሆነ አሁኑኑ የመሳሳሙን ጥያቄ ignore አድርገህ ግንኙነቱን አቁም። ግንኙነቱን አቁም ያልኩበትን ምክንያት ልንገርህ፡ 1 ወደዝሙት የሚገፋፋ ከሰይጣን እንጂ ከእግዚአብሔር ስላልሆነ 2 ጊዜያዊ ደስታን ከሚያስብ ሰው ጋር ትዳር ብትመሰርትም ትዳሩ ስለሚፈርስ 3 ብዙ ፈላጊ ያለው ሰው ለአንተ ተገቢውን ክብር ስለማይሰጥ 4 ድብቅ ግንኙነት ሲታወቅ መዘዙ የከፋ ስለሚሆን #ይህንን_ሁሉ_ተብለህ_ግንኙነቱን_ብትቀጥል_እና_ብትሳሳም_ግን_እድሜልክህን_ለሚበላህ_የፀፀት_እግርእሳት_ተጠያቂ_ነህ። ውድ ወንድምህ
Dec 31, 2022