ሰላም የተወደድክ ወንድሜ እንዴት ነህ? እኔ ደህና ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን! የጥያቄህ መልስ የሚወሰነው በህይወት እያለህ በወሰንከው ውሳኔ ነው። ይህን ስል ምን ማለቴ ነው፡ በሕይወት እያለህ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደግል አዳኝህ አድርገህ ከተቀበልክ ከሞትክ በኋላ የምትኖረው ኑሮ በሕይወት እያለህ ከምትኖረው ኑሮ ይሻላልና ከሞት በኋላ በህይወት ብንኖር ይሻላል። በሕይወት እያለህ ደግሞ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደግል አዳኝህ አድርገህ ካልተቀበልክ ደግሞ ከሞት በኋላ የምትኖረው ህይወት የስቃይ፣ የጭንቀት ስለሆነ ከሞትን በኋላ መኖር አይሻልም። #ውድ ወንድሜ እንዲሁም ይህንን የምታነብቡ ሌሎች እህትና ወንድሞች በሙሉ ከሞት በኋላ መኖራችን ስለማይቀር ከሞትን በኋላ የምንኖረው ህይወት ያማረ፣ የተስተካከለ፣ የቀና እንዲሆን በህይወት እያለን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደግል አዳኛችን አድርገን እንቀበል።
Dec 31, 2022