Selam አንድ ጓደኛ አለችኝ ማለት በስርአት gf ምናምን አይደለም ግን ለ4 ዓመት ምናምን እንተዋወቃለን እና በቃ ሁሌ flirt እናደርጋለን ምናምን ግን እኔ የምር እሷን በጣም እወዳታለሁ እሷ ግን ለኔ ያላትን feeling አላውቅም እና ብነግራት ብንጣላስ ብዬ ፈራሁ እና ወይ ስለሷ ስሜት ማወቅ የምችልበት ወይም indirectly የምጠይቅበት መንገድ ካለ እስኪ pls Thanks❤🙏
Dec 31, 2022ሰላም ውድ ወንድሜ እንዴት ነህ? እኔባለሁበት ቦታ ደህና ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን! ወደመልሴ ከመግባቴ በፊት አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ፡ ልጅቷን በዘላቂነት በትዳር አብሮ ለመኖር ነው የምትፈልጋት? ወይስ ዝምብሎ boyfriend, girlfriend ለመሆን? በትዳር በዘላቂነት አብሮ ለመኖር ከሆነ ሀሳብህ የእሷን ስሜት ከማወቅህ በፊት የእግዚአብሔርን ፈቃድ እወቅ። የእሷን ስሜት ከማወቅህ በፊት የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማወቅ አለብህ ያልኩበትን ምክንያት ልንገርህ፡ 1 የእግዚአብሔር ፈቃድ የሌለበት ትዳር ፀንቶ አይቆይም 2 የእግዚአብሔር ፈቃድ የሌለበት ትዳር ሰላም የለውም 3 የእግዚአብሔር ፈቃድ የሌለበት ትዳር እረፍት የለውም 4 የእግዚአብሔር ፈቃድ የሌለበት ትዳር ደስታ የለውም 5 የእግዚአብሔር ፈቃድ ሳይኖር የገባህበት እጮኝነት የእግር እሳት ነው 6 ያለእግዚአብሔር ፈቃድ የጀመርከው ጓደኝነት ዘላቂነት አይኖረውም ደግሞም እግዚአብሔርን ያሳዝናል 7 ያለእግዚአብሔር ፈቃድ ከገባህበት ጓደኝነት ፀፀት እና ቁጭት ነው የምታተርፈው ስለዚህ ወዳጄ ሆይ የእሷን ስሜት ከማወቅህ በፊት የእግዚአብሔርን ፈቃድ እወቅ። ውድ ወንድምህ
Dec 31, 2022