Hyy family Eski guys mitakutn mirt funny poem(ግጥም) share adergun
Dec 28, 2022ሁለቱ መላጦች ሁለት በራ ሠዎች ሲያልፉ በጎዳና ዕቃ መሬት ወድቆ ብልጭ ሲል ያዩና ተሽቀዳድመው ሄደው ከቦታው ሲደርሱ ተፎካከሩበት ሁለቱም ሊያነሱ። በኀላም ተማተው በጥፊ በጡጫ አንደኛው ነጠቀ በጉልበቱ ብልጫ አገላበጠና ቢመለከት ፈጥኖ ዕቃውን አገኘው ማበጠሪያ ሆኖ። እስኪ ሁላችሁም በሉ ፍረዱት እሱ ራሱ በራ ፀጉር የለበት ሮጦ ተማቶ ቀምቶ ቢያመጣ ምን ያደርግለታል ሚዶ ለመላጣ? ሰዎች ይፋጃሉ አስበው ሳይፈርዱ የተጣሉበትን ጥቅሙን ሣይረዱ ከመጣላት በፊት ከመቀያየም የነገሩን ፍሬ መረዳት መልካም። ከዶ/ር ከበደ ሚካኤል
Dec 29, 2022