✍️ ወንድ ተወለደ.....ለምን ተወለደ? ** በኃጥያት ደዌ ታመን በአለም ተሸንግለን ባይን አምሮት ተታለን እጅግ ተጎሳቁለን ከህግ በታች ሆነን በግዞት ተጥለን በነውር አድፈን ለሞት ተሰልፈን ዛሬ ነገ ሞትን እያልን በቁም ሞተን ካዳኛችን ርቀን ወደ ገዳይ ሸሽተን ያኔ.... ፍቅር ቃሉ የሆነ ፍቅር ግብሩ የሆነ ጠላትነት ይቅር ኑ ወደኔ እያለ በድንቅ ምህረቱ በበዛ ውርደቱ በፍቅር ጥልቀቱ በታምራት ጣቱ በመውደድ ሽንፈቱ በዛ በበረቱ ልክ እንደ ትንቢቱ እጅጉን ከፍ ሊል እጅግ ተዋረደ ድንግሏ ፀነሰች ወንድ ተወለደ ጀግና ተወለደ ጌታ ተወለደ በጨለማ ላሉ ነጋ ጎህ ቀደደ በወልድ የመስቀል ሞት አብ ቁጣው በረደ ሁሉ ሰላም ሆነ ከላይ እርቅ ወረደ በፊተኛው አዳም ከአብ የተጣላ በሗለኛው አዳም ከአብ ተዛመደ #ሄኖክ_አሸብር
Dec 29, 2022