ሰላም ቤተሰብ ምን መሰላቹ እኔ ጎበዝ ተማሪ ነበርኩ:: እና 11ኛ ክፍል እያለው ለኢንተርኔት አዲክትድ እሆናለው ክላስ አልከታተልም ጨዋታ እና ቀልድ ብቻ ነበር የማቀው:: ከዛ ግን ቀስ በቀስ በትምህርቴ በጣም የወረደ ውጤት አመጣው💔 አሁን 12 ነኝ እስከዛሬ ከ 9-12 ያሉ ትምህርቶችን አንዱን እንኳን መጨረስ አልቻልኩም። እባካችሁ ያለኝን ጊዜ እንዴት መጠቀም እችላለው🙏
Dec 28, 2022እየውልህ ጓዴ እኔ እስከ 10ኛ ክፍል ትምህርት የሚባል ነገር ለአይኔ ነበር የምጠላው።30ኛ ና ከዛ በላይ ነበር ደረጃዬ😂 ግን በአንዳንድ ምክንያቶች ለራሴ ያለሁት እራሴ ብቻ መሆኑን አውቄ 11 ላይ ስራዬ ብዬ አጥንቼ የደረጃ ተማሪ መሆን ችያለሁ።አስራ ሁለትንማ ጭራሽ ተወው....በቃ አሉ ከሚባሉት ተማሪዎች መካከል ሆንኩ። entrance ከመድረሱ ሶስት ወር በፊት ጥናት ጀምሬ ውሎዬ ላይብረሪ ነበር።እሁድ የለ በአል የለ!አሁን ስንቶቹ ስለፈተናው በሚያማርሩበትና ተስፋ በቆረጡበት ሰአት positive የሆነ ውጤት ከሚጠብቁት ነኝ።እና ምን ልልህ ፈልጌ መሠለህ....አነሳስህ መድረሻህን አይወስነውም።የትናንት ጉብዝናህ ለentrance አይጠቅምም ። ነቃ በል።"በትናንት በሬ ላይታረስ ዛሬ" ይባላል።
Dec 29, 2022