ለምንድን ነው ግን ሰዉ መታየት የሚፈልገው በተለይ በዚህ ዘመን ያለን ወጣቶች ,ፋራ ላለመባል የማይደረግ ጥረት የለም ጉራማይሌ ቋንቋ መጠቀም በመሀል ኢንግሊሽ ጣል ማድረግ ፣ሰው የለበሰውን መልበስ፣ባስ ላይ ፣ታክሲ ላይ ሶሻል ሚዲያ መጠቀም፣ አያውቅም ወይም አታውቅም ላለመባል ዝም ብሎ መቀባጠር ፣ ተምሯል እንዲባል የግድ ኦኬ ፣ ኖ ማለት ፣ አጉል የበላይነት ስሜት ፣ በተለይ በተለይ ከጎረቤት ከተሞች አዲስ ላይ የምትመጡ ሰዎች ሸገርያንስ ለመባል የማታደርጉት ያላሳለሰ ጥረት እንደሌለ በብሌኔ ነፅሬዋለሁ እነዚህ ነገሮች በመንገዴ ላይ ሲያጋጥሙኝ ቆም ብዬ በውስጤ እስቃለሁ አይ አንድአንዴ ከመንጋ መለየት ጠቃሚ ነው አዬ እድሜ ጠገብ አይደለሁም ግና 20 አመቴ ነው ሸገር ተወልጄ ሸገር ያደኩኝ ልጅ ነኝ የእናንተን ኤክስፒርያንስ ማነው ልምድ ንገሩኝ (ጉራማይልዬዋን አርሙኝ )😁😁
Dec 26, 2022በሐሳብህ የምስማማበትና የማልስማማበት ነገር አለ። የብዙ ወጣቶች ችግራችንን አንስተሃል። በጣም እደግፈዋለሁ። የማልስማማበት ሐሳብህ እንደወጣት፣ ከአፍሪካ ውጭ ተወልጄ ከዛም ኢትዮ መጥቼ አዲስ አበባን ጨምሮ ብዙ ከተሞች ላይ እንደኖረ ወጣት የምነግርህ ነገር አለ። አዲስ አበባ አንተ እና መሰሎችህ የምታወራላቸው ሰዎች ብዙ የሏትም። አዲስ አበባ አዋቂ ነን ባይ መሃይማን ወጣቶች የተጠራቀሙባት፣ ከትንሽ ነገር ጀምሮ መስረቅን እንደ እርድና የሚመለከቱ የበዙባት፣ ከሴት ጋ በአልጋም በጫካም መባለግና ማባለግ ጉብዝና የሆነባት፣ መስራት እየቻሉ ወላጅ ላይ ጥገኛ የሆኑ ያሉባት፣ እናትን እየጠሩ መስደብ ጉብዝና የመሰላቸው፣ የመረረ ጨዋታው በጩቤ እና ኮብል ድንጋይ የሆኑ (አፋርን የሚያስንቁ¡)፣ ፀጉርን አንጨባሮ ስራ ፈት ሆኖ ድንጋይ ማሞቅ ፋሽን የሆነባት የሰገጤዎች መናኸሪያ ከተማ ከሆነች ትንሽ ሰነበተች። ምንም እውቀት ሳይኖረው አዲስ አበባ በመወለዱ ብቻ የእርድና ጥ...ግ ላይ ያለ የሚመስለው ህዝብ ያለበት ከተማ ነው። ይህ አባባሌ ስርአት ያላቸውን ወጣቶች፣ የድሮ አዲስ አበቤዎች፣ መልካም ወላጆችና እንዲህ አይነት የቆሸሸ ባህሪ የሌላቸውን አዲስ አበቤዎች አይመለከትም። ቀሪዎቹ እንዲስተካከሉ ምኞቴ ነው። ለመረጃ: ሌሎች ከተሞች ላይ የምታየው ይህ ባህሪ መነሻው A.A. ነው። በኖርኩባቸው ከተሞች ጓዶቼን ጨምሮ አመዛኙ ባህሪያቸው ወላጅን አክባሪ፣ ሁሉንም ስራ የሚሰራ፣ ምስኪንነቱ አንተ እንዳልከው አዲስ አበባ ደርሶ ሲመለስ እንደ አዲስ ልጅ ልሁን የሚል (😁) ነው። የአዲስ አበባ ልጅ እና የክልል ከተማ ልጅ በምንም መልኩ አይገናኝም። እናንተ ቋንቋን ጉራማይሌ ስላደረጋችሁ ብቻ ሰማይ መልዓክ የማይኖርበት ቦታ ራሳችሁን ሰቅላችኋል። የክፍለ አገሩ ሰው የሸገርን ሰው መብለጥ አለብኝ ብሎ በየከተማው አንገቱን ደፍቶ እየሰራ ተተኩሷል።🔫 ይህን የምታነቡ ሸገሪያንስ ወ አዲስ አበቢያንስ ወ አዳነች አቤቤያንስ ወ ሽመልስ አብዲሳያንስ ተስተካከሉ። መልካም ማክሰኞ!
Dec 27, 2022