✍️ሲጀመር [ባሁን ጊዜ] በቤተክርስቲያናችን 44ቱ ታቦት የሚባል ነገር የለም‼️ ✍️ይህ ታሪክ በተለምዶ ከጎንደር ታሪክ ጋር በተያያዘ በፊት ይባል የነበረ እንጂ ሁሉንም ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተክርስቲያናትን የሚወክል አይደለም። ምክንያቱም ታቦት በቁጥር አይወሰንም በየትም ቦታ ቤ/ክ እስካለ ድረስ መስዋዕት ማቅረብያ ታቦት አለ። even አሁን እራሱ በጎንደር ብናይ በጣም ብዙ አብያተክርስቲያናት ተሰርተዋል። 44ቱ የሚባለው በዘመኑ የነበረውን ሁናቴ እንጂ የአሁኑን አይደለም። ✍️ሌላው ደግሞ የምነግርክ ነገር ማነው ቆይ ታቦት ይመለካል ያለክ❓ወይስ የአንተው አረዳድ ነው❓እንደዛ ብሎ የነገረክ ሰው ካለ ተጠንቀቀው ተሳስቷል። ብዙዎቹ ይህንን ቃል የሚጠቀሙት ሆን ብለው የቤተክርስቲያኒቷን ስም ለማጥፋት ነው። ከእንደዚህ አይነት ሰዎች ተጠንቀቅ። አንድም የሚያውቁት ነገር የለም። ✍️እኛ የምናመልከው እግዚአብሔርን [ሥላሴን] ብቻ ነው።።።።።። ከእግዚአብሔር ውጭ ማንኛውም አምልኮ በቤተክርስቲያናችን ጣኦት ይባላል‼️ ከፈጣሪ በስተቀር ደግሞ እኛ ማንንም አናመልክም። ✍️ታቦት ደግሞ በሐዲስ ኪዳን ቅዱስ ቁርባን መፈተቻ (ለእግዚአብሔር መስዋዕት የሚቀርብበት የተቀደሰ ንዋይ ነው። ስለዚህ ታቦት በቁሙ የእግዚአብሔር ክብር መገለጫ እናም ለፈጣሪ አምልኮ የሚቀርብበት መስዋዕት የሚፈተትበት የተመረጠ እቃ/ንዋይ እንጂ በቁሙ የሚመለክ አይደለም። ✍️ለታቦት ደግሞ ተገቢውን ክብር እንሰጣለን እንጂ አናመልክም‼️‼️‼️ ✍️More ግልጽ እንዲሆንልክ ደግሞ ጠጋ ብለክ እውነተኞቹን የቤ/ክ መምህራንን መጠየቅ ትችላለህ።
Dec 22, 2022