Hey Sibeza Betam overthinker negn ena hulum ngr nw overthink maregew endet nw koy makom mchlew
Dec 19, 2022Makom aychalm love, we just get used to it
Dec 20, 2022Hey Sibeza Betam overthinker negn ena hulum ngr nw overthink maregew endet nw koy makom mchlew
Dec 19, 2022Makom aychalm love, we just get used to it
Dec 20, 2022Overthinking “Overthinking” (ኦቨርቲንኪንግ) የtሰኘውን ቃል ወደ አማርኛችን ስንመልሰው “በሃሳብ ብዛት መዋጥ” ወይም “በሃሳብ ብዛት መወሰድ” ብለን ልንተረጉመው እንችላለን፡፡ ሲተነተንም፣ የትም ልንወስዳቸው የማንችላቸውን ነገሮች እየደገሙና እየደጋገሙ በማሰብ ማውጣትና ማውረድ፣ ከአስፈላጊው በላይና ከመጠን በበዛ ሁኔታ አንድን ነገር ሲያሰላስሉ መዋል ተብሎ ይገለጻል። አንዳንድ ሰዎች አንድን ሃሳብ ከያዙ፣ አንድ መረጃ እጃቸው ከገባ፣ አንድን ነገር ከጠረጠሩ ወይም በአጠቃላይ በአንድ ጉዳይ ላይ ማሰብ ከጀመሩ ያንንው ሃሳብ ይዘውና ሳይለቁ ሲያወጡትና ሲያወርዱት መዋልና ማደር ይቀናቸዋል፡፡ ይህ የአእምሮን ሞተር ካለልክ የሚያሰራ ሂደት በርካታ ለሆነ ክስረት ያጋልጣል፡፡ 1. አእምሯችን ለቁም ነገር እንዳይውል ወጥሮ ይይዘዋል በአንድ ሃሳብ የሚወሰዱ ሰዎች (Overthinkers) ያንን ከማድረጋቸው የተነሳ ሌላ ነገር ማሰብ ስለማይችሉ አእምሯቸውን ተጠቅመው ብዙ ማቀድና መስራት ሲችሉ መፍትሄ የሌለውን ነገር ሲያብሰለስሉ እምቅ ብቃታቸውን ያባክናሉ፡፡ 2. ለጭንቀት ያጋልጣል ሃሳብን የማይለቁ ሰዎች (Overthinkers) ራሳቸውን ለጭንቀት የማጋለጥ ሰፊ እድል አላቸው፡፡ ደጋግመው የሚያስቡት ሁኔታ ወደየት ሊሄድና ምን ደረጃ ሊደርስ እንደሚችል ጥጉ ድረስ ስለሚያስቡ ገና ያልሆነውንና ሊሆን የማይችለውን ሁሉ በማሰላሰል ይጨናነቃሉ፡፡ 3. ለክስረት ያጋልጣል ሃሳብን ማብሰልሰል (Overthinking) ምንም ነገር ብናደርግ መለወጥ የማንችላቸው ነገሮች ላይ እንድናተኩርና ጊዜን፣ የስነ-ልቦናንና የስሜት ጉልበትን፣ እንዲሁም ገንዘብን እንድናባክን ያጋልጠናል፡፡ Overthinker መሆኔን በምን አውቃለሁ? • አንድ ሃሳብ ላይ ከመጠመዴ የተነሳ ሌላ ነገር ማሰብ አለመቻል፤ • ፈታ፣ ዘና ለማለት አለመቻል፤ • ያለማቋረጥ መጨነቅ ወይም መጨናነቅ፤ • ከእኔ ቁጥጥር ውጭ በሆነ ነገር ላይ ማተኮርና እሱን ሲያስቡ ውሎ ማደር፤ • የአእምሮና የስሜት ዝለት ስሜት መጫጫን፤ • ብዙ አሉታዊ ሀሳቦች ማስተናገድ፤ • በአእምሮ ውስጥ አንድን ሁኔታ ወይም ልምምድ እየደጋገሙ ማጫወት፤ • የሁሉንም ነገር በጣም መጥፎ የሆኑ ጎኖች በማሰብ፡፡ ነገርን አለመልቀቅ የለመደውን አእምሯችሁን እንደገና በማለማመድ ነገርን መልቀቅንና መተውን አስተምሩት፡፡ From @Dreyob
Dec 20, 2022መፍትሄዎችን አብረን እንመለከታለን @yoni_xyz መልካም ቀን🙏
Dec 20, 2022