ሰ ላ ም ሰዎች ይሄ ዘፈን የመሰሉ ፋንታሁን ነው ግጥሙ ይሀው ኩታ ትወዳለህ መባሉን ሰምቼ ይኸው እፈትላለሁ ጥጡንም ሸምቼ እንኳን ለሚወዱት አርሶ ለሚጭን ለእንዝርት ይገለጣል የሸጎቹ ጭን እንዝርቴን አንስቼ ሳዞረው ሳዞረው ያመመው ይመስላል የሚያንዘረዝረው ትርጉሙ የገባው ??i think በተሳሳተ መንገድ ሳይሆን አይቀርም የተረጎምኩት😁
Dec 19, 2022I think 3 ena 4gnaw line lay yalew nw mesel confuse yaregesh, ene endegebagn ጥጥ ሲፈተል እንዝርቱን በደምብ ለማዞር ጭናቸውን ከፍተው በውስጠኛው ጭን አስደግፈው ሽርርርር የሚያረጉት ነገር አለ፣ እና ሌላው ደግሞ #አርሶ_ለሚጭን የሚለው ሰምና ወርቅ ያለው ይመስለኛል፣ እህል አርሶ ከዛ ምርቱን እየጫነ የሚሸጥ ትጉ ገበሬ ሲሆን ወርቁ ደግሞ አርሶ(እሷን😁) ለሚያስረግዝ ማለቷ ነው። ስለዚህ የሸጎቹ ጭን ለእንዝርት ብቻ ሳይሆን ለሚወዱት አርሶ ጫኝም ይከፈታል ማለቷ ይመስለኛል።
Dec 19, 2022