ምን መሰላችሁ በቃ ብክት ያለ ህይወት ውስጥ ነኝ በአጭሩ ልንገራችሁና ሴት እና 26 አመቴ ነው በመጥፎ አጋጣሚ ወደ ሱስ ገባሁ የማልጠቀመው የሱስ አይነት የለም drugn ጨምሮ ሀሺሽ ሲጋራ ዊድ ሁሉንም ተመስገን ልበል ለዚህ የሚሆን ገንዘብ አላጣም ከየት እንደሚመጣ ባላውቅም ግን አላጣም በግሩፕ ስለምንጠቀም ከዛም አልፎ ብዙ ድራግ ስለምጠቀም ከዛ ቦሀላ ምን እንደማደርግ አላውቅም በተለያየ መንገድ ከብዙ ወንዶች ጋር እወጣለሁ ህይወት ለኔ ምንም ነው ምንም የሚያጓጓኝ ነገር የለም በመሀል ግን አረገዝኩ የሚገርማችሁ አባቱ ማን እንደሆነ እንኳ አላውቅም እዚሁ ህይወት ውስጥ ሁኜ 2ኛ ወሬ ነው ማርገዜን ያወኩት ይሄን ባወኩ ቅፅበት ግን የሆነ ስሜት ተሰማኝ ምንም እንኳን የልጄን አባት ባላውቀውም ግን የአብራኬ ክፋይ ስጋየ ነውና ለልጄ ትኩረት መስጠት እና ህይወቴን ማስተካከል መቀጠል እንዳለብኝ ም/ክ በዚሁ ከቀጠልኩ ልጄ እንደሚጎዳ አውቃለሁ አንድ ነገር ቢሆንብኝ እራሴን ይቅር አልለውም በዚህ የዘቀጠ ህይወት ውስጥ እንድወልደው አልፈልግም እየወሰድኩ ያለሁትን ሱስ መተው እንዳለብኝ ባውቅም ለኔ ቀላል ሊሆንልኝ ግን አልቻለም ም/ክ የምወስደው ድራግ ከባድ ነው በተለይ ዊዱ አንድ ቀን ላቆመው ሞክሬ ላብድ ምንም አልቀረኝም depression wust እየከተተኝ ነው በጣም ከብዶኛል እና ምክራችሁን እፈልጋለሁ ለኔ አይደለም ለልጄ ስትሉ pls
Dec 17, 2022እግዚአብሔር ይርዳሽ እህቴ። ምን ግዜም በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ እጁን ወደ እግዚአብሔር በመዘርጋት በጸሎት የሚማፀን ሰው አሸናፊ ነው። በዚህም ደግሞ መጨረሻዬን አሳምርልኝ እንደማለት ያለ ትልቅ ጸሎት የለም። በቀደመ ሕይወትሽ ውስጥ የነበሩትን የተበላሹ ኩነቶች በቀጣዩ ሕይወትሽ ውስጥ እንዲኖሩ አለመፈለግሽ መልካም ነው። ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታዎች ናቸውና የጠፋሽ ልጁን በሰጠሽ ልጅ ሊያገኝሽ ወዶ ሊሆን ስለሚችል ለልጅሽ በማለት ለማቆም መወሰንሽ መልካም ነው በዚኽም እግዚአብሔርን በማመስገን ስለቀደመ ስህተትሽ ይቅርታን እየለመንሽ በንስሀ ከመመለስ ብትጀምሪ እግዚአብሔር በቀጣይም ይረዳሻልና አስቀድመሽ ንስሀ ግቢ። በቀጣይ ያለው ነገር እጅግ ከባድ ስለሚሆን እግዚአብሔር ኃይልን ያስታጥቅሽ ዘንድ። እህቴ በምንም አይነት ፈተና ውስጥ ብትሆኚ ምንም ነገር እንዳትፈሪ። ላለመጠቀም ስትሞክሪ የሚሰማሽን ስሜትን ጨምሮ !! በዛን ሰዓት በእንባ እግዚአብሔር ፊት ቁሜ ልጁ እያለቀሰች ዝም የሚል አባት የለም። አይዞሽ። እግዚአብሔር ይርዳሽ።
Dec 18, 2022