#ZEMARIT MESKEREM WOLDE #ዘማሪት መስከረም ወልዴ #የተሻለ ነገር 🌹 የተሻለ ነገር ❤ የተሻለ ነገር አስበህልኝ ነው ፈተናው የበዛው ነገ መልካሙን ቀን አያለሁ በዚህም አምናለሁ አዝ...🌹 ሰው ነኝ መቼም እቸኩላለሁ የሀሳቤን ቶሎ እሻለሁ አዳዴማ በቃ እረስቶኛል እላለሁኝ እኔን ትቶኛል አተ ግን ስጦታህ ብዙ ነው ታደርግልኛለህ በጊዜው አንተኮ አትፈልግም ውድቀቴን ሁል ጊዜ በጭንቀት ማንባቴን አዝ...🌹 አንዱን ቺግር ሳልሻገረው ይደረባል ገዝፎ ሌላኛው የሕይወትን ውጣ ውረድ አይቻለሁ ስንቱን መንገድ ጨለማው ቢረዝም ሌሊቱ አይኔ አይቀርም ብርሃን ማየቱ እሩቅ የመሰለው ይቀርባል ሰላም ወደ ቤቴ ይገባል አዝ...🌹 ፈተናዬ ቢበዛብኝም የሀዘኔ ማብቂያው ቢርቅ አምላክ ባንተ ታሪክ ይሆናል የደስታ ቀን ለኔም ይመጣል አንተ አትሳሳትም በስራህ ፍፁምና መልካም አባት ነህ እስከሚሆን ድረስ ተራዬ እጠብቅሃለሁ ጌታዬ አዝ...🌹 አለፈኮ ዘመኔ እያልኩኝ በማጉረምረም ይሄው አለሁኝ ፅናት ጎሎት ልቤ ቢያማርም ያሰብክልኝ ያልከው አይቀርም አንተ ግን ስጦታህ ብዙ ነው ታደርግልኛለህ በጊዜው አንተኮ አትፈልግም ውድቀቴን ሁል ጊዜ በጭንቀት ማንባቴን 🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺👏👏👏