ሰላም ሰላም በድጋሚ የወጣ የቢዝነስ ማስታወቂያ ማለቴ ጥያቄ። የመልስ ቦታ ላይ መጠየቄን የነገርከኝ ሰው ተባረክ በ 500ሺ ብር ምን ልስራ?
Dec 16, 2022የባረክከው ልጅ አይደለሁም። ግን ጠቁሜህ ልለፍ አነስ ያሉ ነገር ግን አሪፍ ገቢ ሊኖራቸው የሚችሉ ይመስለኛል። 1, የ construction/ግንባታ እቃዎችን ከአዲስ አበባ በህጋዊ መንገድ ትገዛለህ። ቆርቆሮ፣ አሸንዳ ቆርቆሮ... ወዘተ ወደ ክልል እና 'ዞን' ከተሞች (በተለይ ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ያሉ ከተሞች) ትወስደውና አትርፈህ ትሸጠዋለህ። በቅርቡ አዲስ አበባ እና ያለሁበት ቦታ ላይ የግንባታ እቃ ሳነጻጽር ያገኘሁት ልምድ ነው። ለምሳሌ በአሸንዳ ቆርቆሮ በሜትር እስከ 100+ ልዩነት አጊኝቼበታለሁ። በብዛት ብታሰላው ከፍ ያለ ነው። 120 'ሜትር' ልገዛ ፈልጌ በትንሹ የ 10,000 ብር ለውጥ አጊኝቼበታለሁ። ቀሪውን አጣርተህ የሚያዋጣህን ሞክር። 2, በአገር ውስጥ የተሰሩ ብዙ የ'ኤሌክትሪክ' ሃይል የማይፈልጉ (ለቤት የምንጠቀመውን ባለ 1 phase ቆጣሪ የሚጠቀሙ) የዳቦ መጋገሪያ 'ማሽኖች'ን ገዝተህ በግብርም/ከግብርም ነጻ በሆነ መልኩ ቤትህ ውስጥ ዳቦ እየጋገርክ አውጥተህ ማከፋፈል። ይህም ዝምተኛ ሆነህ 'ባንክህ'ን የምታደልብበት አንዱ መንገድ ይመስለኛል። እቃዎቹን (ማቡኪያ፣ ማኮፈሻ፣ መጋገሪያና ሌሎች ትናንሽ እቃዎች) ለመግዛት ቢበዛ 300,000 ቢፈልግብህ ነው። ዳቦ መሸጥ በየትኛውም የአፍሪካ አገር አትራፊ ያደርጋል! 3, ገንዘብህ ከፍ ሲልልህ አንድ መሬት ትገዛለህ። ምጥን ብሎ ፊኒሺንጉ ያመረ ቤት ትሰራለህ። ስትፈልግ ባንክ አስዪዘህ ትበደርበታለህ። ካልሆነም አትርፈህ ትሸጠዋለህ። ወይም ደግሞ ተጀምሮ ያላለቀ ቤት ትገዛና ጨርሰህ በደንብ አትርፈህ ትሸጠዋለህ። በዚህም በዚያም የምመክርህ ልትሰራ ካሰብክ ትኩረትህን service sector and construction sector ላይ አድርግ። እና ምግብ ነክ ነገሮች ላይ። ብዙ ያልተነኩ እና ትንሽ 'ካፒታል' የሚፈልጉ ስራዎች አሉን። ሰው ለምን ድሃ እንደሚሆን ግራ የሚያጋባበት አገር ውስጥ ነን። ከዚህ የተሻለ የሚነግሩህ ካሉ ይጻፉልህ። እኔም ካስታወስኩ እጨምራለሁ። አሁን ባርከኝ😁
Dec 17, 2022