My oromo people's yihe ahun miyabetabten bandira ye oromiya bherawi kelelawi mengst bandira ke oromo hezb ga mnm yemaygenagn betam yemtelut weyane serto yesetachu endhon takalachu?
Dec 12, 2022Wrong. በርግጥ አሁን ያለው የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ስንደቅ ዓላማ orderኡን ቢስትም ክፍለዘመናትን ያስቆጠረ የኦሮሞ ህዝብ መለያ(ፋጂ) ነው። ለማብራራትም ያክል በተለምዶ የአባገዳው ባንዲራ የሚባለው ፋጂ ኦሮሞ በቀደም ተከተል ጥቁር-ቀይ-ነጭ ሲሆን እያንዳንዱ የየራሱ ትርጉም አለው። ጥቁር- ህዝብን በሚጠብቀው አምላክ ይገልጻል። ቀይ- በደማቸው ሃገርን በሚጠብቁ ሰዎችን ይመሰላል። ነጭ- በምክራቸው በተግሣጻቸው ትውልድን በሚቀርጹና ሃገርን በሚያስተዳድሩ ሽማግሌዎች ይገለጻል። ዳግመኛም፤ ጥቁር አምላክን፣ ቀይ ኃይልን፣ ነጭ ደሞ በጥበብ ይመሰላል። አንተ እንዳልከው የ30 ዓመት ብቻ ታሪክ ያለው ሳይሆን ቢያንስ ከ500 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ አርማ ነው። ይህም እንደ አፍሪካ ቀንድ የመጀመርያው ህዝባዊ አርማ ያረገዋል። ባይሆን፤ አሁን የሚሰቀለው የክልል ባንዲራ ያስቀመጥነውን order ያለው ሳይሆን ቀይ-ነጭ-ጥቁር ነው። As any Oromo, ይሄንን ቀደም ተከተል አለመከተሉ ደስ የማያሰኝ ቢሆንም ባንዲራ ጨርቅ ነው። ነገ ተስማምተንበት ልንለውጠው እንችላለን። ከጨርቅ በፊት መለወጥ ያለብን የህዝቡን ስነልቦና፣ የኑሮና የትምህርት ሁኔታን ነው። በዚህ 50 ዓመታት በጣም አንገብጋቢ የሚባሉት መሠረታዊ የኦሮሞ ህዝብን ችግር ለመፍታት ተችሏል። የኦሮሞ ህዝብ መሠረታዊ ችግር የባንዲራ ልሙጥነት ወይም የሾላ ምልክት ጉዳይ ሳይሆን፥ ትልቁ ችግር የነበረው አለማንበብ አለመማር አለመጻፍ ነው። እናም ባሁን ሰዓት አብዛኛው Qubee Generation ማንበብ እና መጻፍ ይችላሉ። So, አሁንም ቢሆን ቅድሚያ ሊሰጥ ለሚገባው ቅድሚያ ይሰጥ የሚለው የአብዛኛው ህዝብ አመለካከት ነው። ስለዚህ "ታቃላችሁ?" ብሎ መጠየቅ ሳይሆን ያለብህ፤ "የሚባለው ነገር እውነት ነው እንዴ?" ብለህ ብትጠይቅ ጥሩ ነበር።
Dec 12, 2022